በአዲስ አበባ ከተማ የ2017በዓ.ም የ8ኛ ክፍል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በአዲስ አበባ ከተማ የ2017በዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 88.8 % ያህሉ 50% እና ከዛ በላይ በማምጣት ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ አስታወቁ።

ኃላፊው በዛሬው እለት  የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤትን በማስመልከት ለተለያዩ የመንግስትና የግል የመገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል። 

በከተማ አስተዳደሩ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በየአመቱ መሻሻል በማሳየት ላይ መሆኑን ኃላፊው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫው ጠቁመው በ2017 ዓ.ም ፈተናውን ከወሰዱ 70,525 ተማሪዎች መካከል 88.8 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች 50% እና በላይ አስመዝግበው ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን አስታውቀዋል።

ዶክተር ዘላለም አያይዘውም  የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤታማ እንዲሆን ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ሴክተሩ ትኩረት በመስጠት የትምህርት ቤት ምገባን ጨምሮ የደንብ ልብስ እና ሌሎች ተጨማሪ የትምህርት ግብአቶች ማቅረቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸው  በየትምህርት ቤቱ የማጠናከሪያ ትምህርትን ጨምሮ  ተማሪዎች በቴሌቪዥን የሚማሩበት አማራጭ መመቻቸቱ እና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራታቸው ለውጤቱ መገኘት ተጠቃሽ ምክንያቶች መሆናቸውን አመላክተዋል።

ዘንድሮው በከተማ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ 20 ተማሪዎች መካከል 13 የሚሆኑት በእቴጌ መነን የልጃገረዶች እና በገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤቶች የተማሩ መሆናቸው አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ  የተቋቋሙበት አላማ ስኬታማ መሆኑን እንደሚያሳይ ኃላፊው በመግለጫቸው ጠቁመው የዘንድሮው ውጤት በ2016 ዓ.ም ከነበረው የ78.9% ወደ 88.8% ማደጉን በመግለጽ  መምህራንን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ተማሪዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.