የአዲስ አበባ የመንገድ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ የመንገድ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ግንባታ እየተፋጠነ ነው፤

አዲስ አበባ ከተማን እንደስሟ ውብ እና አበባ ለማድረግ እየተተገበሩ ካሉ ሥራዎች መካከል አንዱ በተመረጡ የከተማዋ አካባቢዎች እየተከናወነ ያለው የመንገድ ኮሪደር ልማት ግንባታ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በከተማዋ አራት የመንገድ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ ያሳለፈው የካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው 3ኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባው ነበር።

የመንገድ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶቹም፦

• ከአራት ኪሎ በመስቀል አደባባይ እስከ ቦሌ ድልድይ (7 ኪ.ሜትር)

• ከቦሌ አየር መንገድ እስከ መገናኛ ዳያስፖራ አደባባይ (4.9 ኪ.ሜትር)

• ከመገናኛ ዳያስፖራ አደባባይ በአራት ኪሎ በኩል የዓድዋድል መታሰቢያ አካባቢ ድረስ (6.4 ኪ.ሜትር)፣ እና

• ከፒያሳ ዓድዋድል መታሰቢያ ዙርያ፣ በለገ-ሃር ሜክሲኮ፣ በሳርቤት በኩል እስከ ወሎ ሰፈር (10 ኪ.ሜትር) ናቸው።

እነዚህ የመንገድ ኮሪደር ልማቶች ሁለንተናዊ የመንገድ ዘመናዊነትን ያሟሉ ከመሆናቸውም በላይ ዓለም አቀፍ የስማርት ሲቲ ስታንዳርድን በማሟላት የከተማዋን ደረጃ ከፍ የሚያደርጉ ናቸው።

ፕሮጀክቶቹ አዋሳኝ የወንዝ ተፋሰሶችን ያቀፉ፣ የብስክሌት እና እግረኛ መንገዶች፣ የከተማዋን ማስተር ፕላን ታሳቢ ያደረጉ እና ሌሎችም ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮችን ያካተቱ ናቸው።

የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የፕሮጀክቶቹን አፈጻጸም ከዋና የትኩረት አቅጣጫዎች አንዱ በማድረግ ሥራው በቀን 24 ሰዓት በሳምንት 7ቱንም ቀናት (7/24) እንዲሠራ የቅርብ ክትትል በማድረግ ለግንባታው መፋጠን ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።

ለከተማዋ የመንገድ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶቹ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የንግዱ ማኅበረሰብ፣ የፌዴራል እና የከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት ተቋማት ድጋፍ እና አጋርነት ለፕሮጅክቶቹ መፋጠን የራሱ የሆነ አዎንታዊ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.