" ቱሪዝም ለሰላም ! "

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

" ቱሪዝም ለሰላም ! "

ብዝሀ ተፈጥሮ ያላት ኢትዮጵያ ለቱሪዝም ዘርፍ የተመቸች ናት። ሀገራችን የታሪክ ሀብታም ናት።

ተፈጥሮ በሁሉም አይነት የአየር ፀባይ እና መልክአም ምድር የኳለቻት ውብ ሀገር አለችን።

ህብር ባህሎቻችንም ድምቀቶቻችን እና ውበቶቻችን ናቸው። ብዝሀ ማንነቶቻች በአግባቡ በማስተናገድና በመንከባከብ የሀገራችን ዕድገት ማስፈንጠሪያ ለማድረግ በተለይም ከለውጡ በኋላ አበረታች ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ።

በዓለም ለ45ተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ37ተኛ ጊዜ " ቱሪዝም ለሰላም " በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የዓለም የቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ በከተማችን በዛሬው ዕለት ማክበር የጀመርነው የቱሪዝም ሳምንት በተለይም በከተማችን እየተመዘገበ ያለው ፈጣን ዕድገት ለዘርፉም ማንሰራራት ጉልህ አዎንታዊ ሚናውን መወጣት መጀመሩን በማብሰር ጭምር ነው።

ከተማችንም ሀገራችንም ከቱሪዝም ዘርፍ መጠቀም ባለባቸው ልክ ተጠቃሚ ሳይሆኑ ቆይተዋል። በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን የተተገበሩ የገበታ ለሸገር ፣ የገበታ ለሀገር እና የገበታ ለትውልድ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች እና አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ ለማድረግ የተጀመሩ ብርቱ ጥረቶች የቱሪስት መዳረሻዎችን በማስፋት ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ከፍ ማድረግ ጀምረዋል፡፡

ባለማናቸው የቱሪዝም መሰረተ ልማቶች ላይ የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ሀላፊነት የተጣለባቸው የመንግስት ተቋማት ዘርፉ ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ደረጃ ከፍ እንዲል ይበልጥ መስራት ይኖርባቸዋል።

አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ የከተማ ስታንዳርድ እንድታሟላ በኮሪደር ልማቱና በሌሎችም የጀመርናቸውን ስራዎች በማጠናከረ የኮንፈረንስ ቱሪዝም አቅሟንም ለማጎልበት ህዝባችንን አስተባብረን የምናደርገውን ርብርብ አጠናክረን እንቀጥላለን ።

:-አቶ ሞገስ ባልቻ

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.