በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ስራ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ እና የቂርቆስ ክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ የኢድ አልፈጥር በዓልን ከአቅመ ደካሞች ጋር አክብረዋል።

ከተመጋቢዎች ጋር በዓሉን ያከበሩት አቶ ጥራቱ በየነ የታላቁን የረመዳን ፆም የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን እጅግ ኢትዮጵያዊነት በተገለጠበት አግባብ በመረዳዳትና በአብሮነት በማሳለፍ ለዛሬው በዓል በመድረሳቸው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዓሉን ስናከብር ሀይማኖታዊም ኢትዮጵያዊም እሴታችንን ጠብቀን በመረዳዳትና በአብሮነት ሊሆን ይገባል ያሉት አቶ ጥራቱ ይህንንም በዛሬው ማዕዳችን አሳይታችኋልና ይህንን ላስተባበራችሁ ሁሉ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል።

የምንሰራው ስራ ሁሉ ሰውን ታሳቢ ያደረገ ነውና ለሀገር ውለታ የሰሩ ዜጎች እድሜያቸው ሲገፋና ማህበራዊ ችግሮች ሲገጥማቸው ብቸኝነት እንዳይሰማቸው ከጎናቸው መቆም አለብን ያሉት አቶ ጥራቱ እርስ በርሳችን ስንተባበር በርካታ ችግሮችን መቅረፍ እንችላለንም ብለዋል።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ብቻ በዛሬው እለት በ4 የምገባ ማዕከላት ከ2 ሺህ በላይ አቅመ ደካሞችን በዓሉን ምክንያት በማድረግ መመገብ መቻሉን የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ ገልፀዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.