በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰብሳቢነት የሚ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰብሳቢነት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ100 ቀናት ግምገማ ቁልፍ የሆኑ ሴክተሮችን አፈፃፀም በጥልቀት በመመልከት ማካሄድ ጀምሯል።#PMOEthiopia

ከግምገማ መድረኩ በተጓዳኝ ከ2010 እስከ 2015 ዓመተ ምህረት የተላለፉ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎችን የያዘ መፅሃፍ ይፋ ሆኗል። ይህ መፅሃፍ በተጠቀሰው ዘመን የተላለፉ የፖሊሲ ውሳኔዎችን በዝርዝር ያመለክታል። 

 

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ክፍል የሚያከናውነው የመሰነድ ተግባር አንዱ የሆነው ይህ መፅሃፍ ለታሪክ ስነዳ እና መረጃውን ለሚሹ ሁሉ ጠቃሚ የሆነ የሰነድ ዝግጅት ስራ አካል ነው። 

ዛሬ ይፋ የሆነው መፅሃፍ ውስን ቅጂዎች ለፌደራል እና ለክልል ተቋማት የሚሰራጩ ሲሆን መረጃውን ለሚፈልጉ ሁሉ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ድረገጽ ላይ የሚጫን ይሆናል።

#PMOEthiopia


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.