
በጊዜ የለንም መንፈስና በቁርጠኝነት ተነስተን የማህበረሰቡን ተጠቃሚነትና የኑሮ ውድነት እናረጋግጥ ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር
'' ክፍለ ከተማችን ልማቷ ተረጋግጦ ነዋሪዎቿ የሚያቀርቡት የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመፍታት በቁርጠኝነት እንሰራለን'' የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰኢድ አሊ
በፌዴራል ደረጃ ተዋቅሮ በዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ተመርቶ ለተከታታይ 4 ቀናት የቆየው ሱፐርቪዥን በዛሬው ዕለት የከተማ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና የሱፐርቪዥን አባላት በተገኙበት ማጠቃለያ ተደረገ።
የሱፐርቪዥኑ ሉዑካን መሪ የሆኑት ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደገለጹት በልደታ ክፍለ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ ወርደንም በተግባር ምልከታ ያደረግንባቸውና ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገቡ የሚገኙ ስራዎች ማየት ችለናል ከእነዛም መካከል የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት አሰጣጥ፣ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት፣ የስራ እድል ፈጠራ ፣ በት/ት ተቋማት እየተሰሩ ያሉና ተሰርተው የተጠናቀቁ የላብራቶሪ የተማሪዎች ምገባ ማዕከላት እና የህጻናት ማቆያ ፣ የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት ሸማች ማህበራት በቂና ጥራት ያለው የፍጆታ ምርቶችን ማቅረብ መቻላቸው በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሰሩ የመሰረተ ልማትና የበጎ ፍቃድ ስራዎች እንዲሁም ሌሎች በጥንካሬ የታዩ ተግባራቶች ናቸው እነዚህን አጠናክሮ ማስቀጠል ብሎም አዲስ አሰራርንም ማዘመን ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል።
ክብርት ኤርጎጌ ለውጥ ለማምጣት የዜጎቻችንን ችግር ለመቅረፍና መንግሰት የያዘውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ በአንድነት ቁርጠኝነትና በመናበብ መስራት ይኖርባችኋል ያሉ ሲሆን በሱፐርቪዥኑ ወቅትም በአገልግሎት አሰጣጥ በህብረተሰብ ተሳትፎና ና ኑሮ ውድነትን ለመፍታት እንዲሁም ክፍለ ከተማዋን ከወንጀል ነጻ ለማድረግ በሚሰራው ስራ ብሎም በስራ እድል ፈጠራ ላይ በቀጣይ በትኩረት በመስራት ባለሀብቱንና ማህበረሰቡን በማሳተፍ የተጀመሩት ስራዎች በቀጣይ ውጤታማና የህዝብን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ መሰራት አለበት በማለት ገልጸዋል።
የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰኢድ አሊ በበኩላቸው ክፍለ ከተማችን በሁለንተናዊ የልማትና ሰው ተኮር ስራዎች ላይ ውጤታማ እንድትሆን ብሎም በመልካም አስተዳደር የሚነሱ ጥያቄዎቿን ለመፍታት ለነገ የማያድር ስራ እየሰራን ለውጥ እንድታስመዘግብ እየተጋን እንገኛለን በመሆኑም ሱፐርቪዥኑ ያልታዩ ክፍተቶቻችንን ያሳየን በተከናወኑ ስራዎቻችንም ያለንበትን ደረጃ እንድናውቅ ምቹ አጋጣሚ ፈጥሮልናል በቀጣይም በህብረተሰብ ተሳትፎ ስራዎቻችን ፥የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል፥በከተማ ግብርና ቀጣይነት ያለው ስራ ለመስራት እንዲሁም የወጣቶችንና የሴቶችን ስራ እድል ፈጠራ በቁርጠኝነት በመስራት መንግስት የያዘውን የልማት ሰላም በማረጋገጥ የህብረተሰባችንን ችግር የሚፈታ ሰው ተኮር የሆኑ ተግባራትን በቀጣይነት እንሰራለን ብለዋል።
የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮችም ሱፐርቪዥኑ ለእኛ ድጋፍና ክትትል የሚሆን ወደ ኋላ የቀረንባቸውን ሰው ተኮርና የፕሮጀክት ስራዎችን አጠናክረን እንድንሰራ የሚያስችል ነበር እንደዚህ አይነት ምልከታ መደረጉ አስፈላጊ ነው ክትትላቹ አይለየን በባለቤትነትም ለለውጥ በጋራ እንሰራለን ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.