የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተጠሪ ተቋማትና...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተጠሪ ተቋማትና የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት አባላት በመዲናዋ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተጠሪ ተቋማት እና የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።

ጉብኝቱ በከተማዋ የተከናወኑ እና በመከናወን ላይ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን፣ የመልሶ ማልማትና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የልማት ሥራዎችን ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል።

በአዲስ አበባ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች ለነዋሪዎች ምቹ አካባቢ የሚፈጥሩና የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በእጅጉ የሚያሳድጉ መሆናቸውም ተገልጿል።

በተጨማሪም የልማት ሥራዎቹ አዲስ አበባን የተቀናጀ የመሠረተ ልማት የተሟላላት ከተማ እንድትሆን የሚያስችሉ ናቸው ተብሏል።

በከተማዋ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ የአዲስ ዓለም ዓቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል፣ የነገዋ የሴቶች ተሐድሶ ማዕከል፣ የተለያዩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እንዲሁም ሌሎች በርካታ የልማት ስራዎች መከናወናቸው ይታወቃል።

#prosperity


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.