
ከተሞቻችንን የማዘመን ሰፊ ጥረት አይነተኛ ማሳያ የሆነውን በካዛንቺስ ያለዉን የኮሪደር ልማት ክፍል በይፋ መርቀናል።
የተጎሳቆሉ እና በእጅጉ የተጎዱ ቤቶች እና ከባቢ መገኛ የነበረው ካዛንቺስ ዛሬ የጋራ ጥረት እና ለውጥ ሽልማታችን ሆኖ ተገኝቷል። ከዚሁ አካባቢ ተነስተው ለማኅበረሰባችን የከበረ የኑሮ ሁኔታን ለመፍጠር ያለንን ፅኑ እምነት እና ተግባር በሚያሳይ አኳኋን ለኑሮ ወደ ተሻለ ከባቢ የተዛወሩትን ነዋሪዎች ከጥቂት ቀናት በፊት ጎብኝተን ነበር። የተዛወሩበት ከባቢ እጅግ ምቹ መሆኑን አይተናል። ዛሬ ደግሞ የተነሱበትን ሰፈር ድንቅ የኮሪደር ልማት ሥራ መርቀናል።
በአስደናቂ አጭር ጊዜ የተጠናቀቀው የካዛንቺስ ለውጥ ለዘመነ ከተማ ልማት ሥራችን ለአረንጓዴ፣ ንፁህ እና ዘመናዊ የከተማ ማዕከላት ያለንን ርዕይ ግዘፍ ነስቶ በማሳየት መሠረት የሚጥል ነው። በዚህ ግዝፈት የሚከወኑ ሥራዎች ሰፋ ያለ ጥረት ይሻሉ። ጊዜያዊ ምቾት የሚነሱ ፈተናዎችንም ሊያስከትሉ ይችላሉ። ነገር ግን ለታላቁ የሀገር ጥቅም የሚከፈሉ አስፈላጊ መስዋዕትነቶች ናቸው። ይኽ የእድገት መንገድ መቀጠል ያለበት ነው። የታደሰ ተስፋ ይሰጣልና። በተለይ ለልጆቻችን ነገ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.