ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር ያረጋገጥንበ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር ያረጋገጥንበት የካዛንቺስ- ሜክሲኮ- ለገሀር- ቸርችል- እስጢፋኖስ- 4 ኪሎ ኮሪደር ልማትና መልሶ ማልማት ሥራዎቻችን በዛሬው ዕለት መርቀን ለነዋሪዎቻችን ግልጋሎት ክፍት አድርገናል።

የካዛንቺስ ኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራን ስንጀምር በቅድሚያ ያሰብነው ሰውን ሲሆን ነዋሪዎቻችንን ፍፁም ለመኖር ምቹ ካልሆነ ሁኔታ እና አካባቢዎች በማውጣት ምቹ የመኖሪያ አካባቢን ፈጥረን ተጠቃሚ አድርገናል::

በዚህ 1000 ሄክታር መሬት በሸፈነው የካዛንቺስ የኮሪደር ልማትና መልሶ ማልማት ስራ 40.9 ኪ/ሜ  የአስፋልት መንገድ ዝርጋታ፣ 81.9 ኪ/ሜ የእግረኛ መንገድ ግንባታ፣ 20.7 ኪ/ሜ ሳይክል ሌን፣ 15 የህጻናት መጫዎቻ ቦታዎች፣ 8 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ 16 የህዝብ መዝናኛ ፕላዛዎች እና አረንጓዴ ፓርኮች፣ 19 የመጸዳጃ ቤቶች፣105 የንግድ ሱቆች፣ 40 የመኪና ማቆሚያዎች እና ተርሚናሎች ተካትተው ተገንብተዋል::

105 ሱቆችን በመገንባት ከዚህ ቀደም በአካባቢው  በልማት ለተነሱ ነጋዴዎች እንዲሁም ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ለተመረቁ ሴቶች አስተላልፈናል:: 

ሀገርን የመገንባት ራዕያችን እውን እንዲሆን ልማት የተነሳችሁ ነዋሪዎቻችን፣ በገንዘብ፣ በጉልበት እንዲሁም ሃብት በማስተባበር ሃገር በጋራ ለማነፅ በቅንነት ከጎናችን ለቆማችሁ ባለሃብቶች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች እንዲሁም አመራሮች ሁሉ በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ላደረጉልን  ድጋፍ እና ክትትል በራሴ እና በነዋሪዎቻችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ክንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.