ትላንት ማምሻውን በካዛንቺስ ኮሪደር እና መልሶ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ትላንት ማምሻውን በካዛንቺስ ኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራ ላይ ሃገር የማበልፀግ ራእያችንን በመጋራት በርካታ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችን ፣ እረፍት አልባ የስራ መርሃግር በማሳለፍ አብረዉን ለሰሩ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች ፣አመራሮች ፣ሰራተኞች እና ተቋማትን አመስግነናል::

ከነዚህም መካከል ማሽኖቻቸውም በነጻ ለዚህ ስራ ያዋሱ ባለሃብቶችን፣ ስራ ወስደው በፍጥነትና በጥራት ፕሮጀክቶችን በጊዜ በማጠናቀቅ ያስረከቡ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎችን፣ ይህን ስራ ከጅማሮ እስከ ፍጻሜ በፍጹም ታታርነት እና ቅንነት ያስተባበሩ የከተማችን አመራሮችን፣ የግል የመንግስትና የፌደራል ተቋማትን እንዲሁም የህንጻ ባለንብረቶችን ራዕያችንን በመጋራት ሃገር በመገንባት ስራችን ላበረከቱት ጉልህ አስተዋፅዖ ሁሉ በራሴ እና በነዋሪዎቻችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.