ዛሬ "በፈጠራ ስራ የተካነ ትጉ ትውልድ ለሀገር...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ "በፈጠራ ስራ የተካነ ትጉ ትውልድ ለሀገር ብልፅግና" በሚል መሪ ሀሳብ የአዲስ አበባ ተማሪዎች እና መምህራን የሳይንስና ፈጠራ አውደ ርዕይ በይፋ ከፍተናል።

በከተማችን በልዩ ትኩረት እየተከናወኑ ካሉ የለውጥ ማሳያዎች መካከል አንዱ የሆነው የትምህርት ስርዓታችንን ስብራቶች በመጠገን በቀለም ብቻ ሳይሆን በሚዳሰሱ የፈጠራ ስራዎች የታነፀ ትውልድ የመገንባት ስራዎቻችን ተጨባጭ ፍሬዎች እያፈሩ ይገኛሉ። 

መምህራን ለተማሪዎች የፈጠራ ስራዎች መሰረት ሲሆኑ፣ ተማሪዎች ደግሞ የሀገር ለውጥ መሰረት ናቸዉ። በዚህ ጥረት ላይ የቤተሰብ እና መንግሥት ሚና ከታከለበት በአጭር ጊዜ ውስጥ በሁሉም የለውጥ መስኮች የጠነከረችና የፀናች ሀገር መገንባት ይቻላል። 

ዛሬ በይፋ የከፈትነው የሳይንስ እና ፈጠራ አውደ ርዕይ፣ በተማሪዎች መካከል ውጤታማ ውድድርን ከማስፍን ጎን ለጎን በከተማችን እየተከናወነ ላለው መጠነ ሰፊ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችም  አይነተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ፣ የከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ዘርፉ ላይ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን አና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.