
ካዛንቺስ አካባቢ የነበሩ የልማት ተነሺዎች ዛሬ ማምሻውን በኮሪደር ልማት የተቀየረውን አዲሱን ካዛንቺስ ጐብኝተዋል ፤ ባዩት የልማት ስራ መደሰታቸውን የገለፁበት መንገድ ደግሞ ለቀጣይ ሥራ አቅም ሆኖናል ።
ውድ ነዋሪዎቻችን በጋራ መክረን ፣ በጋራ ስርተን እዚህ ደርሰናል ።
ዉብ ሆና እንደ አዲስ የለማችዋም ካዛንቺስ የናንተ ናት፣ አቃቂ /ገላን ጉራም የእናንተ ነዉ ።
የአዲስ አበባ ዉብ ፅዱ ሆኖ መገንባት ለዛሬና ለመጪው ትውልድ ኩራት ነው !
ሁሌም ኑ ትዝታችሁን አጣጥሙበት ፣ ተዝናኑበት፣ካዛንቺስ ለትውልዱ ስጦታ፣ ለነዋሪው ደስታ እንዲሆን በጎፈቃዳችሁን እና ትብብራችሁ ላልተለየን ለእናንተ በእርግጥ ምስጋናችን የላቀ ነዉ።
ፈጣሪኢትዮጵያእናህዝቦቿን ይባርክ !
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.