ታላቁ የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ በኮልፌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስተባባሪነት የኢፍጣር ፕሮግራም ተካሄደ፡፡
በመርሃ ግብሩም የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ/ዶ/ር፣ ዶ/ር ሼህ ሱልጣን አማን የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዚዳንት ፣ ከፍተኛ የፌዴራል፣ የአዲስ አበባ ከተማና የክፍለ ከተማው አመራሮች እንዲሁም የእምነቱ ተከታዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በዕለቱ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የክፍለ ከተማው አስተዳደር ከመጅሊሱ ጋር ተቀራርቦ መስራቱን ይበልጥ እንደሚቀጥል ገልፀው የኢፋጣር ፕሮግራም ላዘጋጀው ለክፍለ ከተማው አስተዳደር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሼኽ ሱልጣን አማን በበኩላቸው ከከተማ አስተዳደሩ በርካታ በልማት፣ አብሮነትና አንድነትን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ በጋራ እየሰሩ እንደሚገኙ ገልፀው በቀጣይም ይሄንኑ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የክፍለ ከተማው አስተዳደር ከእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጋር በመቀናጀት በርካታ ሰው ተኮር ስራዎች እየሰሩ መምጣታቸውን ገልፀው የክፍለ ከተማው አስተዳደርም የወንድማማችነትና እህትማማችነት በተግባር ይበልጥ በማፅናት የእርስ በርስ ግንኙነታችንን እናጎለብታለን ብለዋል።
የረመዳን ወር የፍቅር ፣የአንድነት ፣የሰላም የመተሳሰብ የአብሮነት እንዲሆንም ዋና ስራ አስፈፃሚ ተመኝተዋል።
በመርሀ ግብሩም አቶ ሳዳት ነሻ በሚንስትር ማዕረግ የፌዴራል ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ፣ አምባሳደር ምስጋናው አርጋ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ፣ አቶ ኬይረዲን ተዘራ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ፣ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ የህ/ተወካዮች ምክር ቤት አባልና ሌሎች የከተማ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.