
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማዉ ከፍተኛ አመራር ጋር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዘጠኝ ወራት የጸጥታ ስራዎችን ገምግመዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመድረኩ ላይ የተናገሩት የከተማዋን እድገት እና ለዉጦች የሚመጥን የጸጥታ መዋቅር ማደራጀት፣ ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር የጸጥታ ስጋት ሊሆን የሚችሉ እንቅስቃሴዎችን ቀድሞ በመለየት፣ ህዝቡን በቀጥታ በማሳተፍና የሰላሙ ባለቤት በማድረግ፣ ወንጀል በመከላከል እንዲሁም ተጠርጣሪዎችን አድኖ በመያዝ በመመርመር እና በማስቀጣት ከተማችንን ሰላማዊ፣ የተረጋጋች እና ለመኖር ምቹ የሆነች በማድረግ በኩል በርካታ ስራዎች በመሰራቱ ዉጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል::
የፀጥታ መዋቅሩ በበኩላቸዉ የከተማ አስተዳደሩ ለፀጥታ አካላት እያደረገ ያለዉ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ትልቅ የሞራል ስንቅ እንደሆናቸው አንስተዉ በከተማዋ የወንጀል መከላከል እና የመቆጣጠር አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱ የከተማው ነዋሪዎች በሰላም ሰራዊት በመደራጀት ያበረከተዉ የላቀ አስተዋፅኦ፣ የሰላም እና የፀጥታ መዋቅር፣ የፓሊስ ሀይል፣ ደንብ ማስከበር እና ሌሎች የፌደራል ፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመሰራቱ መሆኑን ገልጸዋል::
መዲናችንን ከተደራጀ የዝርፊያ፣ ሌብነት፣ ንጥቂያ እና ከየትኛዉም የፀጥታ ስጋት የፀዳች በማድረግ፣ ተቋማዊ ብቃት በማሳደግ ፣የሪፎርም ስራን በማጠናከር፣ የአገልጋይነት ስነምግባር በመላበስ ህብረተሰቡን እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በብቃት በማሳተፍ ፣ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የሰላም ሰራዊታችን እና የደንብ ማስከበር አባላት ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን ይበልጥ በማጠናከር የተገኙ ለውጦችን አጠናክረው እንዲሰሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሳስበዋል::
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.