
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ ማምሻውን የቡልቡላ ፓርክ እና ከቦሌ ኤርፖርት - ካርጎ - ቡልቡላ - አቃቂ ድልድይ ድረስ ያለው የአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጏል::
ከተማችንን ውብ፣ ጹዱ እና ለመኖር ምቹ ለማድረግ የጀመርናቸው ስራዎችን በማጠናቀቅ ከተማችን ፕሮጀክት መጀመር ብቻ ሳይሆን በተያዘላቸው ጊዜ በጥራት እና በፍጥነት ማጠናቀቅ እንደምትችል በማስመስከር ላይ ትገኛለች::
ዛሬ የተመረቀው 21 ሄክታር መሬት የሚሸፍነው የቡልቡላ ፓርክ እና በአጠቃላይ 14 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ከቦሌ ኤርፖርት እስከ አቃቂ ድልድይ ያለው የአረንጓዴ ልማት ስራ በውስጡ ለህዝብ መገልገያ የሚሆኑ በርካታ መሰረተ ልማቶች ተሟልተውለታል::
ከነዚህም ውስጥ:-
• የአረንጓዴ ሥፍራና የመንገድ አካፋይ
• ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳዎች
• የቅርጫት ኳስ፣ መረብ ኳስ እና እጅ ኳስ መጫወቻ ሜዳዎች
• ዘመናዊ የሜዳ ቴኒስ መጫወቻ ስፍራ
• የብስክሌት እና የሩጫ መንገዶች
• የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች
• ፋውንቴኖች እና ፕላዛዎች
• መናፈሻ እና ካፌዎች
• የሕፃናት መጫወቻዎች
• ደረጃቸውን የጠበቁ የመኪና ማቆሚያዎች
• ደረጃውን የጠበቀ ፏፏቴ
• ባሕላዊ ካፌዎች
• ዘመናዊ ካፌዎች
• ጁስ ባር
• አምፊ ቴአትር
• ዘመናዊ የሠርግ እና የሙሽራ ቦታ
• የካምፕፋየር ቦታዎች
• የእግረኛ መንገዶች፣ መብራት እና አደባባዮች
• ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የምግብ መስተንግዶ ቦታዎች
• ከ380 በላይ የሕንፃ እድሳት፣ ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ ሱቆች እንዲሁም በርካታ መሠረተ ልማቶች የተሟሉለት ደረጃውን የጠበቀ የመዝናኛ እና መናፈሻ ሥፍራ ነው፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.