የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አመራሮችና አባላት በከተማችን በፍጥነት እና በጥራት እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶንን እየጎበኙ ነው !

የአዲስ አበባ ፈጣን ዕድገት በህዝባችን ብቻም ሳይሆን ዓለም አቀፍ አድናቆት የተቸረው ፣ አንዳንድ ሀገራትም ተሞክሮውን ለማስፋትም እንደሚፈልጉ እየተናገሩለት የሚገኝ አንፀባራቂ ድል ነው።

የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ያስገኘውን ዘርፈ ብዙ ጥቅም የተረዳው ህዝባችን የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት እንዲፋጠን ቀን እና ሌት 7/24 እየተጋ ከሚገኘው አመራራችን ጎን ተሰልፎ ርብርቡን አጠናክሮ ቀጥሏል።

በዚህም ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት በጥራትና በፍጥነት እየተሰራ ሲሆን በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና በሌሎችም በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች የቅርብ ክትትል የተጠናቀቀው የካዛንችስ ኮሪደር ልማትና መልሶ ማልማት ደግሞ በቅርቡ በክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ለምርቃት በቅቷል።

ካዛንችስ አሁን ላይ በአዲስ የለውጥ ጎዳና ላይ ትገኛለች። ከጥልቅ ጉስቁልና ተላቅቃ የከተማችን ድምቀት መሆን ችላለች።

በካዛንችስ እና አካባቢው የተገነቡ 40 ነጥብ 9 ኪ /ሜ የአስፓልት ፣ 81 ነጥብ 9 ኪ /ሜ የእግረኛ ፣ 20 ኪ /ሜ የሳይክል መንገዶች የህዝባችንን እና የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን አሳልጠዋል።

ለካዛንችስ የልማት ተነሽዎች በተሻለ የመኖሪያ አካባቢ የተሻለ መኖሪያ ቤት የተሰጣቸው ሲሆን ፤ በንግድ ስራ ተሰማርተው ለነበሩት ደግሞ ለካዛንችስ አዲስ ገፅታ የተሻለ የኢኮኖሚ መነቃቃት መፍጠር የሚያስችሉ ሱቆች ተገንብተዋል።

በካዛንችስ እና በአካባቢው የነበሩ የመሰረተ ልማት ችግሮችን የሚያቃልሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን የህዝብ መናፈሻ ፓርኮች ፣ 15 የህፃናት መጫዎቻ ፣ 40 የመኪና ማቆሚያ ፣ 19 መፀዳጃ ቤቶችም ፣ የስፖርት ፓርክ ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎች እና ሌሎችም ተገንብተዋል።

የአዲስ አበባ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
አመራሮች እና አባላትም የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ እያሻሻሉ የአዲስ አበባን ስምና ግብር እያገናኙ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው።

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.