አዲስ አበባ ድህነትን የምትቀርፈው የችግሩን ያህ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባ ድህነትን የምትቀርፈው የችግሩን ያህል ትልቅ መፍትሄ በመሰነቅ እንደሆነ ተገለፀ።

 ይህ የተገለፀው ብሉምበርግ ሲቲስ ኔትወርክ የተሰኘ የመረጃ ገፅ ከተማዋን እና የከንቲባ አዳነች አቤቤን የአመራር አቅም አስመልክቶ ባስቀመጠው ሰፊ ሀተታ ነው። 

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እተከናወኑ ከሚገኙ ሰው-ተኮር ስራዎች ውስጥ ልዩ ነገር አለ፣ ያለው ይኸው የመረጃ ገፅ ይህም የሀገሪቷ ዋና ከተማ ድህነትን ከምትዋጋበት ስራዎች አንዱ ለሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ከሆኑት ውስጥ አንዱ የሆነው ጉዳይ ላይ ማለትም በቀዳማይ-ልጅነት እድገት ላይ አተኩራ እየሰራች መሆኑ ነው ሲል መረጃውን አስፍሯል።

በቅድመ-ልጅነት ጊዜያት የሚከሰቱ የህይወት ክስተቶችም በአእምሮ እድገት ላይ ወሳኝ ናቸው፡፡ እነዚህም በልጆች የትምህርት አቀባበል፣ ጤና እና ባህሪይ ላይ ወሳኝ መሰረትን የሚጥሉ ናቸው፡፡ 

አዲስ አበባም ሁሉም ልጆቿ ሙሉ አቅማቸው ላይ እንዲደርሱ እና አቅማቸውን እንዲጠቀሙ ለማስቻል ከተማዋ በመረጃ ላይ የተደገፈ አቀራረብን በመከተል 12,000 ያህል የመጫወቻ ቦታዎችን በማዘጋጀት፣ 5,000 ያህል የልጆች የእንክብካቤ ባለሙያዎችን በማሰልጠን፣ 1,000 ያህል ቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤቶችን በማደስ፣ እሁድ 120 ያህል ዋና ዋና መንገዶችን በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ ቀን ለትራፊክ ዝግ በማድረግ እና ሌሎችም ተግባራትን በተቀናጀ መንገድ እያከናወነች የምትገኝ ከተማ ናትም ተብሏል።

ይህንንም ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ አዲስ አበባ በአፍሪካ ውስጥ ልጆችን ለማሳደግ የምትመች ምርጥ ከተማ ለመሆን አንግባ የተነሳችውን ራዕይ እውን ለማድረግ እየሰራች ነው ብለዋል ማለታቸውን ጠቅሶ ይህንንም እውን ለማድረግ ከንቲባ አዳነች አበቤ የቀዳማይ-ልጅነት እድገት ስራን በዋናነት በማተኮር አዲስ አበባን እና አፍሪካን ወደፊት በመምራት ላይ የሚገኙ መሪ ናቸው ሲል ብሉምበርግ ከንቲባዋን ገልጻቸዋል።

ይህም ስራ ከንቲባ አዳነች አበቤ ከሌሎች የአፍሪካ አቻ ከንቲባ አመራሮች ኢኒሺኤቲቭ (AMALI) ውስጥ ከሚሳተፉ አመራሮች ጎልተው እንዲታዩ እና እንዲወጡ አስችሏቸዋል ተብሏል። 

በአፍሪካ ዙሪያ ያሉ መሪዎች ወሳኝ አዳዲስ አቅሞችን እንዲያዳብሩ የሚረዳው የመጀመሪያው ትልቅ ፕሮግራም AMALI በኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ከተሞች ማዕከል፣ ቢግ ዊን ፊላንትሮፒ እና ብሉምበርግ በጎ አድራጊዎች መካከል የተመሰረተ አጋርነት ነው።

 እያንዳንዱ ከንቲባ የራሱን ግብ ወይም የአላማ መግለጫ በግልፅ እና በተጨባጭ የሚያሳይ፣ የፍላጎታቸው ደረጃ የሚያንፀባርቅ እና በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚጠናቀቅ በዜጎች ሕይወት ላይ የታሰበውን ተፅእኖ/ለውጥ/ የሚያሳይ እቅድ እንዲያዘጋጅ ይጠበቃል። 

በዚህም መሰረት ከንቲባ አዳነች አበቤ የቀዳማይ-ልጅነት እድገት ስራ ዋነኛ ተቀዳሚ ስራቸው እንደሆነ እና ለውጤታማነቱ እንደሚተጉ አፅንኦት ሰጥተው መናገራቸውን ብሉምበርግ ሲቲስ ኔትወርክ ባሰፈረው መረጃው ላይ አስቀምጦታል ።

በኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ የከተሞች ማዕከል መስራች እና የአማሊ ሊቀ-መንበር የሆኑት ኤድጋር ፒተርስ እንዳሉት ከንቲባዋ በልጆች ላይ ያላቸው ስትራቴጅካዊ ትኩረት እና ራዕይ ብቻ ሳይሆን የሚያሳዩት ርህራሄ እና እንክብካቤ ከሌሎች አቻ የአፍሪካ ከንቲባዎች የተለዩ እንዲሆኑ እስችሏቸዋል በማለት ምስክርነታቸውን አስቀምጠዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.