"የአዲሳ አበባ ነዋሪ በየትኛዉም የልማት ስራዎች...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"የአዲሳ አበባ ነዋሪ በየትኛዉም የልማት ስራዎች ላይ በሃሳብ፤በጉልበት እና በገንዘብ አጋርነቱን በተግባር በማሳየት አሻራዉን አኑሯል፡፡ ይህ ደግሞ በፊት የሌለ አሁን ግን በተግባር እየታየ ያለ ትልቅ ልምድ ብቻ ሳይሆን ላቅ ያለ ክብር የሚሰጠዉ ነዉ፡፡"ክብርት አዳነች አቤቤ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የልማት ስራዎች መሰራታቸዉን እና እየተሰሩ መሆናቸዉን ከኢቲቪ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ገልፀዋል፡፡

ከንቲባዋ በቆይታቸዉ በከተማዋ የተሰሩና እየተሰሩ ባሉ የኮሪደር ልማት እና ሰዉ ተኮር ስራዎች የባለ ድርሻ አካላት ሚና አስመልክተዉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ፅዱ፤ምቹ እና ለኑሮ ተስማሚ እንድትሆን ቀጣዩን ትዉልድ ጭምር ታሳቢ ያደረገ የተለያዩ የልማት ስራዎች በፍጥነትና በጥራት መሰራታቸዉና እየተሰሩ መሆናቸዉን የጠቀሱት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እነዚህ የልማት ስራዎች ተግባራዊ ለማድረግ ከጥናት ጀምሮ በእቅዶቻችን ጭምር የባለድርሻ አካላትን ሃሳብ በማካተት የበኩላቸዉን ሚና እንዲወጡ ተደርጓል ብለዋል፡፡

በዚህም ባለሃብቶች በከተማዋ በሚሰሩ የኮሪደር ልማት እና ሰዉ ተኮር ስራዎች ላይ ገንዘባቸዉን፤ እዉቀታቸዉንና ጉልበታቸዉን ጭምር ሳይቀር ለልማት በማዋል ማህበራዊ ሃላፊነታቸዉን የተወጡ መሆናቸዉንና እየተወጡ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡

ከንቲባዋ ለዓብነትም ሲገልፁ በአንድ ባለሃብት በጀት ወጪ በካዛችስ አካባቢ የስፖርት ኮምፕሌክስ ማለትም የቅርጫት ኳስ፤የእጅ ኳስ፤የልጆች መጫወቻ ሜዳዎች፤የልብስ መቀየሪያ፤መታጠቢያ እና መፀዳጃ ክፍሎች፤እንዲሁም ትልቅ የእግር ኳስ ሜዳ ስፖንሰርነት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዉ እንደ ለሚ ኩራፕሮጀክት ከግላቸዉ በጀት መድበዉ በቦታዎ በመገኘት ቁመዉ ማሰራትም ጭምር የታየበት ነዉ ብለዋል፡፡

በተጨማሪም  የወንዝ ዳርቻ ልማቶችን ላይ እስከ አንድ ቢሊዮን ብር ድረስ የሚያወጣ በጀት በመመደብ በአንድ ባለሃብት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዉ በሌላ በኩልም በምገባ ማዕከል እና በመኖሪያ ቤት ግንባታዎች፤በምገባ ፕሮግራም እና በስራ እድል ፈጠራዎች በመሳተፍ ታሪካዊ ኃላፊነታቸዉን እየተወጡ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡ 

የአዲሳ አበባ ነዋሪ ማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት ባለፈ የምትገነባዉ ሃገሬ ናት በማለት በየትኛዉም የልማት ስራዎች ላይ በሃሳብ፤በጉልበት እና በገንዘብ አጋርነቱን በማሳየት ታሪካዊ አሻራዉን አኑሯል፡፡ ይህ ደግሞ ለእኔ በፊት የሌለ አሁን ግን በተግባር እየታየ ያለ ትልቅ ልምድ ብቻ ሳይሆን ላቅ ያለ ክብር የሚሰጠዉ ነዉ ሲሉም ክብርት አዳነች አቤቤ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.