የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በንድፈ ሐሳብና በመስክ ያሰለጠናቸውን 4ኛው ኮርስ አዲስ ምልምል የሠላም ሠራዊት አባላትን በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታድየም በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል።

በዕለቱ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ  የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እንዳሉት ከህዝብ የተወጣጣና የከተማችን ዋነኛ የሰላም ዘብ የሆነው የሰላም ሰራዊታችንን አሰልጥኖ እንዲመረቅ ማደረግ ከፀጥታ አጠባበቅ ስራ ጎን ለጎን በህዝቦች መካከል መቀራረብን፣በጋራ አጀንዳ ላይ መግባባትና የህዝቦችን ትስስር በመፍጠር አንድነትና ወንድማማችነትን ማጠናከር ዓላማው ያደረገ ታላቅ ተግባር ነው ብለዋል።

ከብሎክ ጀምሮ  በመደራጀት የሰላም ሰራዊት ከፀጥታ ኃይሉ ጋር  በመናበብ ከተማ የሰላምና ልማት ምሳሌ እንድትሆን በዓለም አደባባይ ደምቀን ተውበን እንድንታይ በንድፈ ሀሳብና በወታደራዊ ስልጠና የገነባችሁትን እውቀት ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር ለፀጥታ ኃይሉና ለህብረተሰቡ አቅም በመሆን ኃላፊነታችሁን ተእንድትወጡ አሳስባለሁ ብለዋል ::

አቶ ሞገስ አክለውም የከተማችን ሰላምና ፀጥታ ለመጠበቅ ፣ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥና ልማቱን ለማስቀጠል ጠንካራ የሰላም ሰራዊት አደረጃጀት በመፍጠር ሰላማችን በእጃችን መሆኑን ያረጋገጥንበት ተግባር ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ  ኃላፊ  ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸው ተመራቂ የሰላም ሰራዊት አባላት የፀጥታ አጋዥ ኃይል በመሆን የንድፈ ሀሳብና ወታደራዊ ስልጠና በበብቃት በማጠናቀቅ አደረጃጀቱን በሰው ኃይል በማጠናከር ህብረተሰቡን የሰላሙ ባለቤት ለማድረግ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን የሚያሳይ ነው ካሉ በኋላ ኃላፊዋ አክለውም የከተማው ሰላምና ልማት እንዲጠበቅ የፀጥታ መዋቅሩን  ሌትና ቀን ከብሎክ ጀምሮ ነዋሪውን በማሳተፍ በህግ ማቀፍ የተደራጀ የሰላም ሰራዊት በከተማዋ ሰላምና ደህንነት አይተኬ ሚና እየተጫወተ ነው።

በተጨማሪም የአደባባይ ሁነቶች ሀገር አቀፍና ከተማ አቀፍ ኮንፈረንሰችን ሰላም በማድረግ በሀገር ፍቅርና አብሮነት አርያ ከሆነ ነባር አባላት ጋር በመቀናጀት አኩሪ ተግባራችሁን እንድትወጡ አዲስ ተመራቂ የሰላም ሰራዊት አባላት ትልቅ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል እንደምትወጡትም የፀና እምነት አለኝ ብለዋል።

የቢሮ ም/ል  ሀላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ እንደገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017 ዓ.ም 11,000 አዲስ የሰላም ስራዊት አባላት ለተከታታይ 10 ቀናት በንድፈ ሐሳብና በመስክ ወታደራዊ ስልጠና በብቃት ዝግጁ መሆናቸውን በመግለፅ ለስዚህ ስኬት ተባባሪ የነበሩ ተቋማትንና ግለሰብችን በማመስገን ለሰላም ለፍቅርና ለአብሮነት በቁርጠኝነት መዘጋጀት ይገባል ብለዋል።

አቶ ሚደክሳ አክለውም ተመራቂዎች ለቀጣይ ተልዕኮ ራሳችሁን አዘጋጁ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ስልጠናው የተሳካ እንዲሆን የጎላ አበርክቶ ለነበራቸው ተቋማትና ግለሰቦች በክብር እንግዶች እውቅናና ሽልማት ተበርክቷል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.