
በዚህ ዘመን ቴክኖሎጂን መጠቀም እና አለመጠቀም የመኖርና ያለመኖር እንጅ የምርጫ ጉዳይ አይደለም -አቶ ፍቃዱ ተሰማ
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማስተባበሪያ ዘርፍ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አሰራርን ለማጎልበት እያከናወናቸው የሚገኙ የቴክኖሎጂ ስራዎችን የፌዴራል እና በየደረጃው የሚገኙ የከተማችን አመራሮች በተገኙበት አስመርቋል።
በብልፅግና ፓርቲ ዋናው ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት አዲስ አበባ ቃልን በተግባር የሚለው የብልፅግና ፓርቲ መለያ እሳቤ በጥራትና በብቃት እየተተገበረባት የምትገኝ ከተማ መሆኗን የኮሪደር ልማቱን እና ሌሎች በልማትና በሰላም የተሰሩ ስራዎችን እንደማሳያ ጠቅሰው በፓርቲም ስራዎችን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ የተከናወኑ ተግባራት አድናቆት የሚቸራቸው መሆኑን አስገንዝበዋል።
መደመርን መንገድ ፣ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ደግሞ መዳረሻ በማድረግ በግብርናው ፣ በኢንዱስትሪ ፣ በቱሪዝም በቴክኖሎጂ እና በሌሎችም አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ያወሱት አቶ ፍቃዱ በዚህ ዘመን ቴክኖሎጂን መጠቀም እና አለመጠቀም የመኖርና ያለመኖር እንጅ የምርጫ ጉዳይ አለመሆኑን ገልፀዋል።
ፈተናን ወደ ድል በመቀየር ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ እና ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ አበረታች ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን የጠቆሙት ኃላፊው ግዙፍ አደረጃጀት እና 11 የሚሆኑ የአፍሪካ ሀገራት ያላቸውን የህዝብ ቁጥር ያህል አባላት ያሉት ብልፅግና ፓርቲም የቴክኖሎጂን አቅም በአግባቡ መጠቀም ግድ እንደሚለው አስረድተዋል።
አዲስ አበባ በኮሪደር ልማት እና በሌሎችም ለኢትዮጵያ ብቻም ሳይሆን ለአፍሪካም ተምሳሌት እየሆነች እንደምትገኝ የጠቀሱት አቶ ፍቃዱ የፓርቲ ስራዎችን ለማሳለጥ በከተማችን አየተተገበሩ የሚገኙ ቴክኖሎጂዎችን ተሞክሮ ክልሎችም እንዲቀምሩት በማድረግ እንደ ሀገር እንደሚሰፋ ጠቁመዋል።
በብፅግና ፓርቲ ዋናው ፅ/ቤት የስትራቴጅክ ዘርፍ ኃላፊ
አምባሳደር ሀሰን ብልፅግና ፓርቲ ሀሳቦቹን በተግባር አያረጋገጠ እንደሚገኝ ገልፀው በቴክኖሎጂም በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤቱ ፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎችም እየተመዘገቡ የሚገኙ ውጤቶችን የማስፋት ስራ እንደሚከናወን አስረድተዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ የሀገራችንን የፖለቲካ ስብራት የሚያቃና የሀሳብ ውቅያኖስ ያለው ብልፅግና በሀሳብ ፣ በአደረጃጀት እና በአሰራር የደረጃ ፓርቲ መሆኑን ጠቅሰው ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመንገባት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ብልፅግና ፓርቲ ከተማችንን ስማርት በማድረግ የአፍሪካ ተምሳሌት ለማድረግ ቆርጦ ስለተነሳ የውስጠ ፓርቲ አሰራሩን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል።
ስራዎቻችን በዘመናዊ የመረጃ አያያዝ አቀናጅቶና አደራጅቶ ለመያዝ የሚያስችለው ERP ፣ የአመራር ምዘናውን ዲጂታል ለማድረግ የተፈጠረው እና ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የአመራር ምዘና የአሰራር ሲስተም እና ስማርት ኮንፈረንስ ሩምን የመሳሰሉ በቴክኖሎጂ የታገዙ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ያስረዱት አቶ ሞገስ ይበልጥ እንዲሰፉ መረባረብ እንደሚገባ አስረድተዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማስተባበሪያ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድ አብዱልረሂም የፓርቲ ስራዎችን በቴክኖሎጂ ለማገዝ Enterprise Resource planning / ERP / ፣ የአመራር ምዘና ፣ የመረጃ አያያዝ ሲስተም ፣ ስማርት ኮንፈረንስ ሩም እና መሰል አሰራሮች ወደ ተግባር መግባታቸውን ገልፀዋል።
ሁሉንም የፓርቲ ስራዎች ዲጂታላይዝድ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የጠቀሱት አቶ መሀመድ በተለይም የፓርቲ መረጃዎችን በተቀናጀ መልኩ ለመያዝ ፣ ተጨባጭ ሪፖርቶችን ለመስራት እንዲሁም የሁኔታ ዳሰሳ ለማድረግ የሚያግዘው ERR ሲስተም ይስተዋሉ የነበሩ በርካታ ችግሮችን እንደሚያቃልል አብራርተዋል።
ዘርፉ በየጊዜው ወደ ተግባር እያስገባቸው ለሚገኙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ውጤታማነት የድርሻቸውን እየተወጡ ለሚገኙ ክ /ከተሞች እና ሴክተር ተቋማት በፕሮግራሙ ላይ የእውቅና እና የምስጋና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በፕሮግራሙ ላይ አሰባሳቢ የብሔራዊነት ትርክትን ከፍ የሚያደረጉ ውብ ህብር ዝማሬዎችም በህፃናትና በታዳጊዎች ቀርበዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.