
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ በ4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር አሸናፈ ሆነ
ቢሮዉ በተሳተፈባቸዉ የዉድድር መስኮች ከፍተኛ ዉጤት በማምጣት በ1ኛ ደረጃ አጠናቅቆ አሸናፊ ሆኗል።
በ4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ቢሮዉ በሰልጣኝ ዘርፍ በ19 የሙያ ክህሎት አይነቶች ፣ አሰልጣኝ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ፣እንዲሁም በቴክኖሎጂዎች፣በአሰልጣኝ 1 ቴክኖሎጂ፣ በሰልጣኝ 1 ቴክኖሎጂ እና በኢንተርፕራይዝ 1 ቴክኖዎሎጂ በድምሩ 3 ቴክሎጂዎች ላይ ተሳታፊ እንደሆነ ታዉቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ በእነዚህ በተሳተፈባቸዉ የዉድድር መስኮችም በአጠቃላይ 10 የወርቅ ሜዳሊያ፤ 4 የብር ሜዳሊያ፤ 4 የነሀስ ሜዳሊያ በድምር 18 ሜዳሊያ በማግኘት በ112 አጠቃላይ ነጥብ 1ኛ ደረጃ በመውጣት ሀገር አቀፍ ውድድሩን አሸናፊ በመሆን አጠናቋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.