
በመዲናዋ ከ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የፋይዳ ምዝገባ አድርገዋል
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የፋይዳ ምዝገባ ማድረጋቸው ተመላክቷል፡፡
"ፋይዳ ለኢትዮጵያ" የ 5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
መርሐግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በክብር እንግድነት ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በኢትዮጵያ ብሄራዊነትን ለማቀንቀን ትልቅ ታሪክ ያለው የትርክት የበላይነት ለማምጣት የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑን ተናገረዋል፡፡
ስለ ሀገር መዘመር፤መስራት እና መሮጥ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ኃላፊነት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ 5 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የፋይዳ ምዝገባ መከናወኑን እና ከ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
መርሐግብሩ አገልግሎቱን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማስፋፋት እና ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሚያግዝም አንስተዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.