የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየደረጃው የሚገ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች " ለሀገር ብልፅግና የሁሉም ሚና " በሚል ርዕስ ለውጥን በማፅናት ሂደት ላይ በሚኖሩ የመሀሉ ዘመን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች ተስፋዎችና ተግዳሮቶች ላይ የጋራ ግንዛቤ ፈጥረዋል።

ለሀገር ብልፅግና የሁሉም ሚና!!

ስኬቶቻችንን ለላቀ ድል መስፈንጠሪያ አድርጎ በመጠቀም ውጤታማነትን ማሳደግ ተገቢ ነው !

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች " ለሀገር ብልፅግና የሁሉም ሚና " በሚል ርዕስ ለውጥን በማፅናት ሂደት ላይ በሚኖሩ የመሀሉ ዘመን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች ተስፋዎችና ተግዳሮቶች ላይ የጋራ ግንዛቤ ፈጥረዋል።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በውይይቱ ላይ እንዳስገነዘቡት ስርዓታዊ ሽግግሩን ተከትሎ በርካታ ድሎች እና ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልፀው ስኬትን ተከትሎ ሊኖር የሚችል መዘናጋት ትጋታችንን እንዳይጎዳ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አመላክተዋል።

ህዝባችንን ከጎናችን አሰልፈን ብዙ ተግዳሮቶችን እና ፈተናዎችን መሻገር ቢቻልም ከተሟላ ስኬት ላይ ለመድረስ የተፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎችን በአግባቡ በመጠቀም የከተማችንን እና የሀገራችንን ተወዳዳሪነት ማሳደግ እንደሚገባም አስረድተዋል።

ተቋማዊ አቅምን በማዳበር የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የሚደረገውን ርብርብ ማጠናከር እንደሚገባ የጠቀሱት አቶ ጃንጥራር አሰባሳቢውን የብሔራዊነት ትርክት የማስረፅ ጉዳይም ዋናው የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ገልፀዋል።

በኢኮኖሚው ፣ በፖለቲካውና በሌሎችም ተፅዕኖ ፈጣሪነትንና ውጤታማነትን ለማሳደግ የሚደረገውን ቅንጅታዊ ርብርብ ማጠናከርና አገልግሎት አሰጣጡ ላይም እመርታዊ ለውጥ ማስመዝገብ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ሀገራዊ ለውጡ እውን ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እየተጋ የሚገኘው የለውጡ መንግስት ዛሬም የሰላም እጆቹ እንዳልታጠፉ የተጠቀሰ ሲሆን ፤ ፍላጎቶቻቸውን በጠብመንጃ ለማሳካት የተሳሳተ መንገድ እየተከተሉ የሚገኙ ቡድኖች ጭምር ወደ ሰለጠነ የውይይት መድረክ የሚመጡበትን ዕድል ለማመቻቸት የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠላቸው ተመላክቷል።  

ህዝባችንም ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የሚያደርገውን የማይተካ ሚና ሊያጠናክር እንደሚገባው ተጠቅሷል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በየደረጃው የሚገኘው አመራር ወቅታዊና አዳዲስ እሳቤዎችን የጋራ ማድረጉ የጋራ ግንዛቤ ፈጥሮ ተቀናጅቶ ለመረባረብ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።

ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚደረገውን ጉዞ ለማፋጠን በዳበረ የስራ ባህል ቀን ከሌት 7 / 24 የሚደረገውን ትጋት ተናቦና ተሰናስኖ በመስራት ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባም አቶ ሞገስ አስገንዝበዋል።

አመራሩ የተመዘገቡ ድሎችን እንደ መስፈንጠሪያ በመጠቀም በአገልግሎት አሰጣጡና በመልካም አስተዳደር ላይ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን እንዲሁም በፓርቲያችንም ቀይ መስመር ተብሎ የተቀመጠውን ሌብነትን በመታገል ለሁለንተናዊ ብልፅግና መረባረብ እንደሚገባውም አሳስበዋል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት በርካታ ፈተናዎችን በመሻገር ዕዳዎችን ወደ ምንዳ በመቀየር በየዘርፉ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መመዝገባቸውን ያወሱት አስተያየት ሰጪዎች የሀገራችን የማንሰራራት ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሚናቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.