
በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ደንብ የተላለፉ ተቋማት 1.5 ሚሊየን ብር ተቀጡ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በለሚኩራ ክፋለ ከተማ ወረዳ 03 ኖህ ሪል እስቴት ከተቋሙ ግቢ የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ከወንዝ ጋር በቀጥታ በማገናኘታቸው በተደጋጋሚ በተፈጠረላቸው በግንዛቤ እና በተወሰደባቸው የገንዘብ መቀጮ ተምረው ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እና ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ባለመቻላቸው በዛሬው እለት ከአካባቢ ጥበቃ፣ ከሰላም ፀጥታ እና ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት በሪከርድ የጥፋቱ እጥፍ 800,000 ብር መቀጣቱ አስታወቀ።
በተመሳሳይ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ሁለት ተቋማት ደንብ ቁጥር 180/2017 ተላልፈው በመገኘታቸው 700,000 በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል።
በአጠቃላይ በዛሬው እለት በክፍለ ከተማው ደንብ ቁጥር 180/2017 ተላልፈው በተገኙ ሶስት ተቋማት ላይ በተወሰደ እርምጃ 1,500,000 ብር መቀጣታቸው ገልጿል።
ባለስልጣኑ በከተማው ከአሁን በፊት ተቀጥተው ከድርጊታቸው የማይቆጠቡ ተቋምና ግለሰቦችን በሪከርድ የቅጣቱ እጥፍ በመቅጣት የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
ተቋሙ ለከተማው ነዋሪዎች ማንኛውም የደንብ መተላለፎች ሲያጋጥሙ ለደንብ ማስከበር ባለስልጣን በነጻ የስልክ መስመር 9995 ጥቆማ እንዲያደርስ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
መረጃው፡- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.