በፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ መሰረት “ቃልን በ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ መሰረት “ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና” በሚል መሪ ሃሳብ ከተማ አቀፍ ማጠቃለያ ኮንፈረንስ እያከሄድን ነው።

ፓርቲያችን፣ በባለፉት ሁለት ተኩል የምርጫ ዘመን አጋማሽ ዓመታት አባላቱን እና አመራሩን አቀናጅቶ በመምራቱና ሕዝቡን በቀጥታ በማሳተፉ አበራታች ዉጤቶች አስመስግቧል ።

የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በምርጫ ዘመን አጋማሽ በአፈፃፀሞቻችን የተገኙ ስኬቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ቆም ብሎ መመዘንና መፈተሸ አስፈላጊ ነው።

በባለፉ ሁለት ተኩል ዓመታት አንፀባራቂ ድሎችን ስናስመዘግበ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ አልነበረም።

በርካታ ፈታኝ ሁኔታዎችም ገጥመውናል። መሻገር የቻልነዉ በያዝነዉ የፖለቲካ ዓላማ ጽናት በመርህ ላይ ቆመን በመታገላችን ነው። ፈተናዉን መቋቋም ያልቻሉ ከረጅሙ የትግል ጉዞ ገና በማለዳዉ ተለይተዉናል።

ሀሳባችን የጠራ፣ ዓላማችን ሁለተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ፣ ለመጪዉ ትዉልድ ዕዳን ሳይሆን ምንዳን ማስተላለፍ በመሆኑ በየምዕራፉ የሚገጥሙን መሰናከሎች ለጊዜዉ ሊፈትኑን ይችሉ ይሆናል ከመዳረሻ ግባችን አያደናቅፉንም።

ቃላችንን ጠብቀን ህዝባችንን በታማኝነት ማገልገላችንን እንቀጥላለን ! 

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.