"ትምህርት በመምህራን ይቀረፃል ፤ ሀገር በትምህ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"ትምህርት በመምህራን ይቀረፃል ፤ ሀገር በትምህርት ይበለፅጋል "በሚል መረሃሳብ የአዲስ አበባ ትምህርት ማህበረሰብ ውይይት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አመራሮች እና የከተማችን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የውይይት መድረኮቹን አካሄድ ተዘዋውረው የተመከቱ እና ሂደቱን ያበረታቱ ሲሆን ፤ ለሀገር እድገት የሚጠቅሙ ሀሳቦች ይነሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።

በውይይቱ ላይ በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚያስተምሩ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እና የከተማችን ከፍተኛ አመራሮች በአንደኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ተዘዋውረው ምልከታ አድርገዋል::

ውይይቱን አስመልክተው ማብራሪያ የሰጡት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ከመምህራንና ከትምህርት አመራሮች ጋር በየአመቱ መሰል ውይይቶች እንደሚካሄድ ገልፀው ውይይቶቹ ለስራ ውጤታማነት ትልቅ እገዛ እንደነበራቸው ያብራሩ ሲሆን እየተካሄደ የሚገኘውም ውይይት የጋራ መግባባት ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

የትምህርት ልማት ስራ የሁሉንም ባለድርሻ አካላትን ርብርብ ይጠይቃል ያሉት ሀላፊው ትውልድን በመቅረፅ ስራ ውስጥ በቅንጅት ስራዎች ከተለያዩ አካላት ጋር እየተከናወኑ ይገኛሉም ብለዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.