
በአዲስ አበባ የሚገኙ የትምህርት ማህበረሰብ “ትውልድ በመምህራን ይቀረፃል፤ሀገር በትምህርት ይበለፅጋል "በሚል መሪ ቃል በ11 ዱም ክ/ከተማ ሲያካሂዱት የነበረዉ ዉይይት መጠናቀቁ ተገለፀ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በመሪ ሃሳቡ ከመምህራንና ከትምህርት አመራሮች ጋር ለሁለት ቀናት በ 11 ዱም ክፍለ ከተሞች ሲያካሂደዉ የነበረዉን ዉይይት በዛሬዉ እለት በስኬት ማጠናቀቁን ገለፃል፡፡
የቢሮዉ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እንደገለፁት በሁሉም ክ/ከተሞች ባሉ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚያስተምሩ መምህራንና የትምህርት አመራሮች በተሳተፉባቸዉ መድረኮች ነፃና ዲምክራሲያዊ የሆኑ ዉይይቶች መከናወናቸዉን ተናግረዋል፡፡
የዉይይቱን ዓላማ ሲገልፁም ትምህርት የብዙ ባለድርሻ አካላት ቁርጠኛነት እና እርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ ተቀናጅቶ በመስራት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ዉጤትን ለማላቅ እንዲሁም በዘላቂነት የተሻለች ሃገርና ትዉልድን ለመገንባት ከምንም በላይ የማይተካ ሚና ያለዉ በመሆኑ ነዉ ብለዋል፡፡
አያይዘዉም ከትምህርት ማህበረሰብ ጋር መወያየት ማለት ስለሃገር፤ስለ ትዉልድ መወያየት መሆኑን ጠቁመዉ ከዚህ አኳያ ከማንም በላይ ትልቅ ሃላፊነት ያለብን መሆናችንን አዉቀን ታሪካዊ አደራችንን መወጣት ይጠበቅብናል ሲሉ ገልፀዋል፡:
ቢሮዉ መሰል ዉይይቶችን በየዓመቱ በማድረግ ለትምህርት ዉጤታማነት ትልቅ እገዛ እንደነበራቸዉና አዳጊ ለዉጦችንም በጋራ ማስመዝገብ መቻሉን የጠቆሙት ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ዛሬም የተደረጉ ዉይይቶች የጋራ መግባባት ለመፍጠር፤የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ለማሳደግ፤የአዲሱ ትምህርት አዋጅ አተገባበር ላይ ያሉትን ተሞክሮዎች ይበልጥ ከፍ ለማድረግ፤ህፀፆችን በየደረጃዉ ለመቅረፍ እና ት/ቤቶች የታለመላቸዉን ግብ ለማሳካት ያስቻለ ነዉ ብለዋል፡፡
አክለዉም ሃገርና ትዉልድ ማበልፀግ እና መሻገር የሚቻለዉ በትምህርት ስርዓቱ ዉስጥ ትቤ/ቶች የተጣለባቸዉን ኃላፊነት በአግባቢ ሲወጡ ነዉ ያሉት የቢሮ ኃላፊዉ ለዚህም ተቋማት በሚጠበቅባቸዉ ልክ እንዲገኙ አስፈላጊ በመሆኑ ዉይይቱ የዚሁ ክፍል መሆኑን እና በዘሌቄታዊነትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል፡፡
በመጨረሻም ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ፤ዲሞክራሲያዊ ዉህደትን መፍጠር የተቻለበትና የሚታዩ ህፀፆችን ለመቅረፍ እና ለዉጤት በጋራ የምንታትርበት ትልቅ አቅም የፈጠረ ዉይይት መሆኑን ጠቁመዉ በበጀት ዓመቱ የታዩ ዉስንነቶችንና በትምህርት ማህበረሰቡ የተነሱ ጥያቄዎችን በእቅድ በማካተት በየደረጃዉ በተቀናጀ አግባብ ለመፍታት ያላሰለሰ ጥረት እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡
የዉይይቱ ተሳታፊዎችም በበኩላቸዉ የትምህርት ተቋማት፣ መምህራና ባለድርሻ አካላት በትምህርቱ ዘርፍ ሀላፊነታቸው በአግባቡ እንዲወጡ የውይይቱ መድረክ ሚናው የላቀ መሆኑን ገልፀዉ ት/ቤቶች የታለመላቸዉን ዓላማ ለማሳካት፤ሁለተናዊ ስብእና የተሟላ ትዉልድ ለመፍጠር እና የሃገር እድገት ለማፋጠን የሚያስችል ጭምር መሆኑን አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.