የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ፒያሳ አካባቢ ይኖሩ ለነበሩ የልማት ተነሽዎች ምትክ ቦታ ሰጠ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት የመንገድ ኮሪደር ልማት ስራና የስማርት ሲቲ ግንባታ በከተማዋ እየተከናወነ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በአራዳ ክ/ከተማ ከአድዋ ሙዚየም ( ፒያሳ ) እሰከ ቀበና ድረስ የመንገድ ኮሪደር ስራ ለ24 ሰአት በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ለልማት ስራው የሚያስፈልጉ ቦታዎች ላይ በተለይም ፒያሳ አካባቢ ነዋሪ ለነበሩና በልማት ምክንያት ለተነሱ 136 የግል ይዞታ ለነበራቸው ነዋሪዎች በመሬት አስተዳደር የካሳ መመሪያ በ79/2014 መሰረት ከ75 ካሬ እስከ 2017 ካሬ ድረስ ዕጣ እንዲያወጡ በማድረግ በለሚኩራ ፤ ጉለሌና የካ ሳይቶች ላይ አስረክቧል፡፡
የአራዳ ክ/ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድወሰን ባንጃው እንዳሉት በዛሬው መርሐ ግብር ከፒያሳ ለተነሱ የልማት ተነሽዎች የቦታ ዕጣ ማውጣት መሆኑን አንስተው ተነሽዎቹ የልማቱ ተሳታፊዎችና ደጋፊዎች በመሆናቸው ምስጋና አቅረበዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም በልማቱ ምክንያት የተነሳ ማንኛውም ነዋሪ የካሳ መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት እንደሚስተናገድ ተናረዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.