በመዲናችን በተለያዩ ጤና ተቋማት የሚሰሩ የጤና...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በመዲናችን በተለያዩ ጤና ተቋማት የሚሰሩ የጤና አመራሮችና ባለሙያዎች በከተማዋ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎበኙ

በ 11ዱም ክፍለ ከተሞች በተለያዩ ጤና ተቋማት የሚሰሩ የጤና አመራሮችና ባለሙያዎች በከተማዋ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ተዘዋዉረዉ ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱም ጤናማ ትውልድ ለመገንባት ምቹ የመኖሪያ አካባቢን ለመፍጠር የሚያስችሉ የተለያዩና በርካታ የልማት ስራዎች መሰራታቸዉን እና እየተሰሩ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን እነዚህም ትውልድን ታሳቢ ያደረጉ ዘመን ተሻጋሪ የልማት ስራዎች መሆናቸዉ በተደረገዉ ገለፃ ተመላክቷል፡፡

የጉብንቱ ዋና ዓላማም መንግስት ከለዉጡ ማግስት ጀምሮ ለጤናዉ ዘርፍ ትኩረት በመስጠት ቅድመ መከላከል እና አክሞ የማዳን ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ በተለይም የጤና ተቋማት ተደራሽነትና ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ የተገነቡና እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች ማሳያ መሆናቸዉን በመገንዘብ የጤና ባለሙያዎች ሚናቸው የጎላ በመሆኑ የበኩላቸዉን አስተዋፅኦ ይበልጥ አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ለማስቻል መሆኑን ተገልፃል፡፡

በተጨማሪም እነዚህ በርካታ እና የተለያዩ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች በ24/7 የስራ ባህል በፍጥነትና በጥራት የተገነቡበትና የታደሱበት እንዲሁም ሰፊ የስራ እድል የተፈጠረባቸዉ በመሆናቸዉ ሁላችንም ከዚህ ልምድና ተሞክሮ ወስደን በተሰማራንበት የሙያ መስክ የድርሻችንን እንድንወጣ የሚያደርግ መሆኑንንም ያለመ ነዉ ተብላል፡፡

የጤና አመራሮች እና ባለሙያዎች በጉብኝታቸው መንግስት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተለያዩ ግዙፍ ማህበራዊ አገልግሎቶች የሚሰጡ ፕሮጀክቶችን በመገንባት የህዝቡን የልማት ፍላጎቶች ለማሟላት እያደረገው ያለው ጥረት የሚበረታታ እና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን ጠቅሰዉ ልማቱ በሙያቸዉ ለሃገርና ለትዉልድ የሚጠቅም ስራ ይበልጥ ለመስራት አነሳስቶናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በከተማዋ ባሉ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የተጠናቀቁና በመጠናቀቅ ላይ ያሉ በርካታና የተለያዩ የኮሪደር ልማት ስራዎችን እና  ሠዉ ተኮር ፕሮጀክቶችን መጎብኘታቸዉ ታዉቋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.