“የተደራጀ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ የሀገራዊ መግባ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“የተደራጀ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ የሀገራዊ መግባባት ካስማ ፤የትውልድ ግንባታ መሠረት ነው"በሚል መሪ ሀሳብ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች የማህበረሰብ አንቂዎች እና የሚኒሚዲያ አባላት የመዲናችንን የልማት ስራዎች እየጎበኙ ይገኛሉ፡፡

በጉብኝቱም ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚሰሩ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የማህበረሰብ አንቂዎች እና የሚኒሚዲያ አባላት ተሳታፊ ሲሆኑ ፤ በ11 ዱም ክፍለ ከተሞች የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የተለያዩና በርካታ የልማት ስራዎችን ተዘዋዉረዉ እየጎበኙ መሆናቸዉ ታዉቋል፡፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም  መለስ በጉብኝቱ  ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ  እንደተናገሩት ከተማችን አዲስ አበባ ለችግር የማይበገሩ አመራሮች እና የኮሙኒኬሽን እና የሚዲያ ሠራዊት ይዛ የነዋሪዎቿን ህይወት ለመቀየር እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን ቀን ከሌት እየተጋች መሆኗን የተገኙ ስኬቶች ህያው ምስክር መሆኑን ገልፀዋል ።

እንደ ኮሙኒኬሽን እና የሚዲያ ሠራዊት የሀሳብ  ምንጭ ሆነን ፤ የከተማችን ብሎም የሀገራችን በሀሳብ የሚያምን እና  የሚሞግት ትዉልድ ለመፍጠር ሚናችን የጎላ  መሆኑን ልንረሳ እደባም ብለዋል ። ዛሬ በምንጎበኛቸዉ  በከተማዋ የተሠሩና እየተሠሩ ያሉ በርካታ እና የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በማስተዋወቅና ህዝባችንን የልማትና የብልፅግና ጉዞ አጋር በማድረግ ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ ተግተን ኃላፊነታችንን እንድንወጣ በማለት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም ከዚህ ጉብኝት በኋላ ከ 4ሺ በላይ ከሚሆኑ የሚዲያ አካላት ጋር  ውይይት እንደሚደረግ የቢሮ ኃላፊዋ ጠቁመዋል።

በከተማዋ የተጠናቀቁና በመጠናቀቅ ላይ ያሉ በርካታና የተለያዩ የህዝብ መዝናኛ አገልግሎቶች እና የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ተርሚናሎች፣ፖርኮች ፣ የተለያዩ የንግድ ዘርፎችን ያቀፉ ማዕከላት ፣ታሪካዊ ቅርሶች እና አደባባዮች፣ የመኪና፣የእግረኛ እና የሳይክል መተላለፊያ መንገዶች ፣ የወንዝ ዳርቻ ልማቶች  እና ሠዉ ተኮር  ፕሮጀክቶች የፅናት እና የብርታት ምስክሮች በመሆናቸው በጉብኝቱ የተካተቱ  ናቸዉ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.