የተሳሳቱ መረጃዎችን መታገል ሃገር ወዳድ ከሆነው...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የተሳሳቱ መረጃዎችን መታገል ሃገር ወዳድ ከሆነው የሚዲያ ባለሙያ እንደሚጠበቅ ተገለፀ

"የተደራጀ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ የሃገራዊ መግባባት ካስማ ፤ የትውልድ ግንባታ መሰረት ነው" በሚል መሪ ቃል የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የሚዲያ ባለሙያዎችና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የጋራ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ ላይ የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ  አቶ ሞገስ ባልቻ፣ የሚዲያው የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም አጠቃላይ የሚዲያ ባለሙያው ተሳትፈዋል።

በውይይቱም ላይም የተሳሳቱ መረጃዎችን መታገል ሃገር ወዳድ ከሆነው የሚዲያ ባለሙያ እንደሚጠበቅ የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ተናግረዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈፃሚው በሃገር እና በከተማ ደረጃ ለተመዘገቡ ውጤቶች የሚዲያ ባለሙያው አስተዋፅኦ የላቀ መሆኑን በማውሳትይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።

የሚዲያ ባለሙያው የሙያ ሥነ-ምግባርን የጠበቁ ተዓማኒ መረጃዎችን ለህዝቡ ተደራሽ ማድረግ አለበት ያሉት አቶ ካሳሁን ጎንፋ ፤ ከጋዜጠኞች ከወገንተኝነት የፀዳ እንዲሁም ሙያ እና ህዝብን መሰረት ያደረገ ዘገባ እንደሚጠበቅ አጽዕኖት ሰጥተዋል፡፡

"የተደራጀ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ የሃገራዊ መግባባት ካስማ ፤ የትውልድ ግንባታ መሰረት ነው" በሚል መሪ ቃል የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የሚዲያ ባለሙያዎች እና አመራሮች  ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ ላይ በከተማና በሃገር አቀፍ ደረጃ በልማት፣ በሠላም፣ በዲፕሎማሲ፣ በትምህርት፣ በመልካም አስተዳደር እና በሌሎችም ዘርፎች በተመዘገቡ በርካታ ዉጤቶች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ነዉ ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.