.png)
“የተደራጀ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ የሀገራዊ መግባባት ካስማ ፤የትውልድ ግንባታ መሠረት ነው"በሚል መሪ ሀሳብ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች ፣የማህበረሰብ አንቂዎች እና የሚኒሚዲያ አባላት ዉይይት እያካሔዱ ይገኛሉ
በ 11ዱም ክፍለ ከተሞች ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚሰሩ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የማህበረሰብ አንቂዎች እና የሚኒሚዲያ አባላት በዛሬዉ እለት ዉይይት እያካሔዱ ሲሆን በሁሉም መድረኮች የጋራ መግባባት በመፍጠር የተገኙ ውጤቶችን የሚያፀኑ ፣ ከችግሮች በላይ የሚያቆሙ ፤ ሚዛናዊ አስተሳሰብ የሚያስፍኑ ጠንካራ ሀሳቦች የተነሱበት እና የቀጣይ አቅጣጫ የሚቀመጥበት ዉይይት እንደሚሆን ይጠበቃል።
የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ተገኝተዉ ዉይይቱን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት በከተማ ደረጃ በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሠማሩ የከተማችን ነዋሪዎች ጋር ዉጤታማ ውይይቶች መደረጋቸዉን ጠቅሠዉ የዛሬዉ ዉይይትም የዚሁ አንዱ አካል ነዉ ብለዋል።
አክለዉም በየደረጃዉ ያሉ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሠራዊት የሀሳብ ልዕልናን በትዉልድ ላይ ለማስረፅ ሚናቸዉ የጎላ መሆኑን ተገንዝበን ለከተማችን ሁለተናዊ እድገት በዘላቂነት ለማስቀጠል ዋጋችን ብዙ ነዉና ለትዉልድ ያለንን ዉድ ስጦታ እናበርክት በማለት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።፡
በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከ 4ሺ በላይ የሚሆኑ የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ አካላት በዉይይቱ እየተሳተፉ መሆናቸዉ ታዉቋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.