
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፈረንሳይ ፣ ፓሪስ ያደረጉት የኢንደስትሪ ጉብኝት በቴክኖሎጂ እና የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ላይ ያተኮረ ነበር።
ከልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን 'ስቴሽን ኤፍ' የተባለውን በአለም ትልቁን የግል የቴክኖሎጂ የስታርት አፕ የቢዝነስ መፍጠሪያ ማዕከልን ጎብኝተዋል። የኢትዮጵያ ስታርት አፕ ከባቢ ገና በጅምር ደረጃ ያለ ቢሆንም የቴክኖሎጂ እውቀት ጠገብ በሆኑ ወጣቶች የተሞላ እንዲሁም ጠንካራ አቅም እያሳየ በማደግ ላይ ባለ የዲጂታል ትስስር እየተመራ የሚገኝ ነው። መንግሥት እንደ “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ያሉ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ፈጠራን ለመደገፍ ርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል። ይኽም ለስታርት አፕ ከባቢ በተለይም በፋይናንስ ቴክኖሎጂ፣ በግብርና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በኢ-ኮሜርስ ግብይት አስቻይ ሁኔታን ለመፍጠር ያለመ ነው። በተጨማሪም የ'ስታርት አፕ' አዋጅ የተሰኘ ሁሉን አቀፍ አዋጅ በማውጣት ለስታርት አፕ እንቅስቃሴዎች የህግ እና ተቋማዊ ማዕቀፎችን በማበጀት ውስን የሆነውን የገንዘብ አቅርቦት የሚያሰፋ፣ የቁጥጥር ተግዳሮቶችን እና መሰል ፈተናዎችን ለማለፍ የሚያስችል ሁኔታ ፈጥሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትር በ5G እና 6G ቴክኖሎጂ፣ በሳይበር ደኅንነት፣ በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ እና የኦፕቲካል ትስስር ማዕከል የሆነውን የኖኪያ-ፈረንሳይ ዋና መሥሪያ ቤትንም ጎብኝተዋል። ጉብኝቱ የfiber sensing አቅርቦት፣ የኃይል ቁጠባ ብልሃት እና የ5G ላብራቶሪዎች ምልከታን ያካተተ ሲሆን ይኽም በዘርፉ ፈጠራ፣ መሠረተ ልማት ግንባታ እና ዘርፍ ዘለል ትብብሮች ላይ ለኢትዮጵያ ዋጋ ያላቸው ትምህሮቶች የተገኙበት ነበር።
በመጨረሻም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ፈረንሳይን የሚገኘውን ታሌ የምርምር እና ቴክኖሎጂ መዐከል ጎብኝተዋል። ይኽ በብዝሃ ዘርፍ የሚንቀሳቀስ የታሌ ግሩፕ የምርምር ተቋም የኩባንያው አለምዓቀፍ የምርምር ጥረት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ የሚያገለግል ማዕከል ሲሆን በኤሮስፔስ፣ መከላከያ እና አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ መስኮች ላይ ያተኩራል።
እነዚህ ጉብኝቶች የአለምዓቀፍ ግንኙነቶችን የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር በማፋጠን ሀገራችንን የአፍሪካ የፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ማዕከል ለማድረግ በማመቻቸት ረገድ የእውቀት ልውውጦችን አስፈላጊነት አስምረው የሚያሳዩ ናቸው።
#PMOEthiopia
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.