" መንግስት የህዝቡን የልማት ተሳትፎ ያሳየበ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

" መንግስት የህዝቡን የልማት ተሳትፎ ያሳየበት፣ በጋራ መልማትንና መጠቀምን ያፀናበት እንዲሁም ያሉንን ፀጋዎች በአግባቡ መጠቀም መቻልን ያረጋገጠበት በመሆኑ እንደሀገር ልንኮራበት የሚገባ ነዉ ። "የንግዱ ማህበረሰብ''

 'የንግዱ ማኀበረሰብ ሚና ፤ ለሁለንተናዊ ብልፅግና''በሚል መሪ ሀሳብ በከተማ ደረጃ  በመዲናችን ያሉ የንግዱ ማህበረሰብ  የከተማዋን የልማት ስራዎች  ጎበኙ ::

በከተማችን አዲስ አበባ  የተጠናቀቁና በመጠናቀቅ ላይ ያሉ የልማት ስራዎችን የመዲናዋ የንግዱ ማህበረሰብ  በዛሬዉ እለት ተዘዋዉረዉ ጎብኝተዋል።

ጎብኚዎችም የካዛንቺስ ኮሪደር ልማት ፣አለም አቀፋ ኮንቬንሽን ሴንተር፣አቃቂ የልህቀት ማዕከል፣ገላን ጉራ የተቀናጀ መንደር፣አድዋ ድል መታሰቢያ፣የቸርቸርና የሜክሲኮ ኮሪደር ልማት፣ልደታ የበጎነት መንደር፣ላፍቶ በራስ አቅም የተሰራ የልማት ስራዎች፣የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ ጉለሌ የተቀናጀ ልማት መንደር፣ቦሌ ኤርፖርት ካርጎ እንዲሁም  የነገዋ ሴቶች ማዕከልንና የልበ ብሩህ ት/ቤት ሠዉ ተኮር ፕሮጀክቶችን እና የመንገድ  መሠረተ ልማቶችን  መጎብኘታቸዉ ታዉቋል።

ጉብኝቱም  ከተማዋ በምታመነጨዉ ገቢ  የከተማዋን ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚያረጋግጡ  የተቀናጁ ዘርፈ ብዙ የልማት  ስኬቶች አስመዝግባለች ። ይህም በቀጥታ  በንግዱ ማህበረሰብ የላቀ ተሳትፎ  ትልቅ ድርሻ እንደነበረው በተጨባጭ ማሳያ ነው።

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ የንግዱን ዘርፍ ለማዘመን እየሰራቸው ባሉ በርካታ ተግባራት የንግዱ ማህበረሰብ  በዘላቂነት የጀመረዉን የልማት አጋርነት ይበልጥ በማጠናከር  ለትዉልድ የሚሻገር የጋራ አሻራን ለማኖር ያለመ መሆኑ ታዉቋል።

ይህም የከተማዋን ገፅታ ከማጉላት ባለፈ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቷን  የሚያጎናፅፍ፤ነዋሪዎቿ  የተሻለ እና ትርጉም ያለዉ ህይወት እንዲኖራቸዉ  በተጨባጭ እያረጋገጥን የመጣንበት ህያዉ የጋራ ድላችን  መሆኑን  ለማመላከት  ጭምር ስለመሆኑም መገንዘብ ተችሏል።

ነጋዴዎች በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለፁት:- ባለፍት የለውጥ ዓመታት የተሰሩ የልማት ስራዎች የሰው ልጅን ክብርና ፍላጎት መሰረት አድርገው የተሰሩ መሆናቸውን በጉብኝታችን ማረጋገጥ ችለናል  ይህም መንግስት ለህዝቡ የገባዉን ቃል በተግባር የፈፀመበት ተጨባጭ ሀቅ ነዉ ብለዋል።

አክለዉም መንግስት  በሀገር እድገትና በትዉልድ ግንባታ ላይ በሚሠራቸዉ ስራዎች የህዝብን የልማት ተሳትፎ ያሳየበት በጋራ መልማትንና መጠቀምን ያፀናበት እንዲሁም ያሉንን ፀጋዎች በአግባቡ መጠቀም መቻልን ያረጋገጠበት በመሆኑ እንደሀገር ልንኮራበት የሚገባ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም መንግስት የንግዱን ስርዓት ለማዘመን እያደረገ ያለዉን ትጋት አድንቀዉ  እንደ ሀገርም ሆነ በከተማ ደረጃ  ሁለተናዊ እድገታችንን ለማፋጠን በሚደረጉ ሁለተናዊ እንቅስቃሴዎች የንግዱ ማህበረሰብ  በገንዘቡ፣በእዉቀቱ እና በጉልበቱ ድጋፉን ይበልጥ በማጠናከር ለቀጣይ ትዉልድ የምትበጅ ሀገር ለመፍጠር ተቀናጅተን እንሰራለን ሲሉ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.