.png)
መምህራንና የትምህርት አመራሮች በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑና እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎበኙ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “ትውልድ በመምህራን ይቀረፃል ፤ ሀገር በትምህርት ይበለፅጋል "በሚል መሪ ቃል ዛሬ በሚካሄደው ከተማ አቀፍ ማጠቃለያ ዉይይት ላይ የሚሳተፉ የመዲናችን መምህራንና የትምህርት አመራሮች የከተማዋን የልማት ስራዎች ጎብኝተዋል።
ጉብኝቱ በአቃቂ ልህቀት ማዕከል ፣ ኢንዱስትሪ ዞን ፣ ገላን ጉራ የመኖሪያ መንደር ፣ ቡልቡላ ፓርክ ፣ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል እና ብርሀን የአይነ ስውራን አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን በጉብኝቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የከተማችን ከፍተኛ አመራሮች ፣ ሌሎች አመራሮች ፣ መምህራንና የትምህርት አመራሮች በመገኘት የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለፁት ትውልድን የሚቀርፁ መምህራን በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ማየታቸው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸዉን የከተማዋን የልማት ስራዎች ለሌሎች አካላት ለማሳወቅ ለልማት ስራው ውጤታማነት የበኩላቸዉን ሚና እንዲወጡ ለማስቻልና ይህንን የሚያውቅና የሚመጥን ትውልድ ለማፍራት ከፍተኛ አበርክቶ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.