.png)
ከWebuild Group ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፔይትሮ ሳሊኒ ጋር በሮም ተገናኝተን እየተሳተፉባቸው ባሉ ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ ተወያይተናል።
በጥቂት ወራት ውስጥ በሚጠናቀቀዉ የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኩራት በሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ እንዲሁም በኮይሻ ግድብ ፈጣን አፈፃፀም እንደታየው ሀገራዊ ግቦቻችንን በማሳካት ረገድ ከWebuild Group ጋር ያለን ትብብር ወሳኝ ነው። በዛሬው ውይይታችን በመሠራት ላይ ባሉት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም፣ በፍጥነት በታገዘ ውጤታማነት ላይ ፈጠራን እና ዘላቂነትን የሥራዎቻችን ማዕከል አድርገን መያዝ እንደሚገባ ተነጋግረናል። ውይይታችን የኢኮኖሚ እድገትን በመምራት እና የረጅም ጊዜ ልማትን በመደገፍ ሀገር የሚያሻግሩ ፕሮጀክቶችን በመከወን ረገድ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ያንፀባረቀ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር)
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.