ዛሬ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ክቡር...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ክቡር መሀሙድ አሊ የሱፍን እንኳን ደህና መጡ ብለን ተቀብለን አነጋግረናል ።

ከኮሚሸነር አሊ የሱፍ ጋር በተለያዪ  የልማት እና የአፍሪካ ከተሞች ትብብርን በሚመለከቱ  ጉዳዮች ዙሪያ ስለ ቀጣይ ስራዎች  የአዲስ አበባ ድርሻ እና አስፈላጊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።

አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና ፣ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቶች ከተማ በመሆኗ  ኩራት የሚሰማት  በመሆኑ እስከ አሁን እያገለገለች ካለችዉ በላይ  ሁሉንም ነዋሪዎቿን እና ተቀማጭ ዲፕሎማት እንግዶቿን ባማከለ መልኩ በትጋት ለማገልገል  ሀላፊነቷን በተሟላ ሁኔታ ለመወጣት እየተጋች እንደሆነ ገልፀንላቸዋል።
ክቡር ሊቀመንበሩ አዲስ አበባን  ተዟዙረው መመልከታቸውን፣ በበአላት እና ምሽት  ጭምር የአዲስ ለአበባ ነዋሪዎች የሥራ ባህል ለውጥ ያላቸውን አድናቆት ገልጸው ፤
የአዲስ አበባ ለውጥ በሌሎች የአፍሪካ ከተሞችም እንዲስፋፋ  ተሞክሮዎችን መቀመር እንደሚገባም ገልፀዋል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.