
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የፍትህ እና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴዉ የ 2017 በጀት ዓመት የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የ 9 ወራት አፈፃፀምን ገምግሟል።
የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ለፍተህ እና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለፁት ቢሮዉ በበጀት ዓመቱ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅሙን ይበልጥ ለማሳደግ እና የተሠጠዉን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት የከተማውን የኰሙኒኬሽን እና የሚዲያ አዎታሩን በከተማዋ አጀንዳ የበላይነት በመምራትመሠራቱን ጠቅሰዋል ።
ቢሮዉ በሰጠዉ ልዩ ትኩረትም አመራሩና ባለሙያዉ ቁርጠኛ አቋም በመያዝ የተጠና እና በእቅድ የታገዘ አሰራር በመዘርጋት እስከታችኛዉ መዋቅር በቴክኖሎጂ የተደገፈ ወጥነት ያለዉ እና የተናበበ ክትትልና ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰዉ አፈፃፀምን መሠረት ያደረገ ምዘና መካሔዱን እና በእቅድና ከእቅድ ተጨማሪ ወቅታዊ አጀንዳዎችን ፣ የተመዘገቡ ስኬቶችን ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ መስራቱን አመላክተዋል።
በክ/ከተማ እና ሴክተር መዋቅሮችም ግብረመልሶችን በመስጠትና ተፈፃሚነታቸዉን በማረጋገጥ በተሠራው ስራ ክፍተቶችን በማጥበብና በማረም በተቋማት መካከል የተቀራረበ አፈፃፀም እንዲኖር መቻሉን ገልፀዉ በዚህም ጠንካራ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሠራዊት መገንባት ተችሏል ብለዋል።
በተመሳሳይም በወረዳዎች ላይ በቅንጅት የተጀመሩ ስራዎች ይበልጥ በማጠናከር የአቅም እና የግብዓት ዉስንነቶችን በመቅረፍ በሙሉ አቅም የሚጠበቅባቸዉን እንዲወጡ የጋራ እርብርብ እየተደረገ ይገኛልም ሲሉ ጠቅሰዋል።
አክለዉም አጀንዳ በመቅረፅ እና በመሸጥ የሀሳብ የበላይነት እንዲኖር በዜና በህትመት በፕሮዳክሽን እና በዶክመንቴሽን የተሠሩና እየተሠሩ ያሉ ስራዎች ሚናቸዉ የጎላ መሆኑን ጠቅሰዉ እነዚህንም በተለያዩ የሚዲያ ፕላት ፎርሞችን የመጠቀም እና ከተለያዩ የሚዲያ አካላት ጋር በመቀናጀት ሁሉንም ማህበረሰብ ያማከለ ስራ መሠራቱን ገልፀዋል።
በዚህም በመረጃ ጥራትና ተደራሽነት እንዲሁም በፈጣን የመረጃ ቅብብሎሽ እና የሀሳብ የበላይነት አዳጊ ዉጤቶች ማስመዝገብ መቻሉንና ይህም በሀገር ዉስጥ ብቻ ሳይገደብ በዉጩ ማህበረሰብም ሆነ ሚዲያ ተፈላጊነቱ እያደገ አመኔታዉ እየጨመረ መጥቷል ሲሉ የቢሮ ኃላፊዋ ተናግረዋል::
የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ እንደገለፁት ቢሮዉ በየጊዜዉ ውስጡን እየፈተሸ የተሠጠዉንም ግብዓት ወደ ተግባር እየለወጠ በበጀት ዓመቱ ከማዕከል እስከ ወረዳ ተቋማማዊ አሠራሮችን እና አደረጃጀቶችን በመዘርጋትና ከቴክኖጂ ጋር በማዋሀድ እንዲሁም ከአመራር እስከ ባለሙያ ቁርጠኝነትን የተላበሠ የተቀናጀና የተናበበ ስራ በመስራት የላቀ ዉጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል ።
አክለዉም የከተማዋን አጀንዳዎች በመቅረፅና በባለቤትነት ግንባር ቀደም ሆኖ በመምራት እና በመሸጥ በከተማዋ የሀሳብ የበላይነት እንዲሰርፅ ከማድረግ ፤የከተማዋን ገፅታ ከማጉላት እንዲሁም የተዛቡ አስተሳሰቦችን ከማረም አኳያ እየተሠራ ያለዉን ተግባር እና የመጣዉን ዉጤት አድንቀዉ ከተማዋ የጀመረችዉን ሁለተናዊ የልማት ስራዎች በማሳለጥ እና የብልፅግና ጉዞዋን በማፋጠን ረገድ የበኩሉን ሚና እየተወጣ ስለመሆኑ ተግባራቱ ተጨባጭ ማሳያዎች ናቸዉ ብለዋል።
የከተማዋን ፈጣን እድገት፣ የህዝቡን የመረጃ ፍላጎት እና የአልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የተዛቡ አስተሳሰቦችን መሠረት ያደረጉ ስራዎች ልዩ ትኩረት ተሠጥቷቸዉ በቅንጅት በመሠራታቸዉ እና በአዳጊ ዉጤት የታጀቡ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ እና ፓለቲካዊ እምርታዎች ማምጣት ተችሏል ሲሉ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ተናግረዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.