
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል።
ኢንስትትዩቱ ከምድር እስከ ህዋ ድረስ የሚገኙ መረጃዎችን በመተንተን የምርምር ስራዎችን የሚያከናውን ተቋም ነው። የምርምር ስራዎቹ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እየተተነተኑ ቅድመትንበያና የትንበያ ስራዎችን በመስራት ለሚመለከታቸው ተቋማት እንዲጠቀሙበት ያስችላል። የጂኦ ስፓሻል ጥናትና ምርምር በተለያዩ ዘርፎች የተዋቀረ ሲሆን ዛሬ በየሥራ ክፍሎቹ የሚከናወኑ የመረጃ ትንተና እና ምርምር ስራዎች ምልከታ ተደርጓል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.