ለውጡ ካፈራቸው ትሩፋቶች አንዱ የሀገሩን ሀብት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ለውጡ ካፈራቸው ትሩፋቶች አንዱ የሀገሩን ሀብት እና ፀጋ ቆጥሮ የሚያውቅ የለውጥ አመራር መፈጠር መቻሉን ነው። ፦ ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለአጠቃላይ ለክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች በአመራር ጥበብ እና በአመራር ውጤማነት ስልጠና ተሰጥቷል።

ስልጠናውን የሰጡት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የመጀመሪያው እውቀት ሀገርን መውደድ ነው፣ ሀገሩን የሚወድ ዜጋ የሀገሩን ሀብት እና ፀጋ ሰፍሮ የሚያውቅ ነው። አመራሩ አቋምና አቅምን በመጠቀም ሀገሩን፣ አከባቢውን ለመለወጥ አሰባሳቢ ትርክትን በመገንባት፣ የሀገራችን ብሄራዊ ጥቅም በማስከበር፣ የኢትዮጵያ ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማስጠበቅ እና እውቅና በመስጠት፣ የብልጽግና እሳቤዎችን በመተግበር ታሪካዊ ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በፕሮግራሙ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ ኢትዮጵያ መበልጸግ አለባት በሚል ቁጭት የጀመርናቸው ሀገራዊ ስኬቶቻችን በማስቀጠል በተከታታይ እየተሰጡ የሚገኙት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የታመቀ ለሀገር የሚበጅ ከገዥ ትርክት ግንባታ ጋር በተያያዘ ያለንን እውቀት ለምንመራው ተቋም ግብአት በመውሰድ እራሳችንን እና ሀገራችን ለመቀየር ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በተከታታይ የሚሰጡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች አመራሩ  በተሰማራበት የስራ መስክ ውጤታማ እንዲሆን አልፎም የሀገራችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ገልጸዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ይከበር ስማቸው ጠንካራ የአመራር ስርዓት ለመገንባት እየሄድንበት ባለው የብልጽግና ጉዞ የብልጽግና ተስፋ አርአያ የሀገራችን እንቁ በሆኑት የፊት አመራሮች ስልጠና መሰጠት መቻሉን ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር ለተግባር ውጤታማነት ከፍተኛ ድርሻ ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

‎በስልጠናው ላይ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ ፣የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ ፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አጠቃላይ አመራሮች ተገኝተዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.