ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን አባቶች በከተማችን እየተከናወኑ ያሉ ግዙፍ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል ። ከጉብኝት በኋላ በፅህፈት ቤታችን ተቀብለን በተለያዩ ከተማ አቀፍ ጉዳዮች እና የጋራ ስራዎች ዙሪያ ተወያይተናል።

ብፁዓን አባቶቻችን ከለውጡ ጀምሮ በከተማችን  መንግሥት ያከናወናቸውን የልማት ስራዎች በመጐብኛት ለተሰሩት ስራዎች ያላቸውን አድናቆት ገልጸው፣ በቀጣይ ጊዜያትም ፈጣሪ ክንውንን እንዲሰጠን በፀሎት እና በቡራኬ እንደማይለዩን ገልጸውልናል።

እኛም የሀገራችን ብቻ ሳይሆን የአህጉራችን መዲና እና የዓለም አቀፉ ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ መናገሻ የሆነች አዲስ አበባችንን ይበልጥ ለመለወጥ ያለንን ቁርጠኝነት እየገለጽን፣ አባቶቻችን በምክር እና ጸሎት ሁልጊዜ ከእኛ ጋር ስላሉ እና ስላበረታቱን ከልብ እናመሰግናለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች  አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.