"ፈጣሪ በባረካት ምድር በሀይማኖት አባቶች እየተ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"ፈጣሪ በባረካት ምድር በሀይማኖት አባቶች እየተባረኩ ለቀጣይ ትውልድ የሚበጅ ስራዎችን መስራት ከመቻል በላይ የሚያስደስት ነገር የለም።" ብፁዓን የሀይማኖት አባቶች

"ሀሳብ  አመንጪዎችንና ሀሳብን ወደ ተግባር ለዉጠዉ   ለትዉልድ ትርጉም ያለዉ ተጨባጭ እድገት ላስመዘገቡ ለዚህም  መንግስትና ህዝብ ለሠሩት ታሪካዊ ስራ ከልብ ሊመሠገኑ ይገባል።"ብፁዓን የሀይማኖት አባቶች

የመዲናችን የሀይማኖት አባቶች በከተማዋ በሁሉም አቅጣጫዎች የተከናወኑ ፈርጀ ብዙ የልማት ስራዎችን ተዘዋዉረዉ ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱም በመዲናዋ ያሉ የሀገራችን  ብፁዓን የሀይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

ብፁዓን የሀይማኖት አባቶች በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት የሠዉ ልጅ ህይወት እና  የከተማ ታሪክ ለመቀየር እንዲሁም የከተማዋን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማፋጠን እንደሀገርም ሆነ ከተማ አቀፍ ስራዎችን መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከህዝቡ ጋር በአጋርነት መስራቱ ለስኬቱ ማሳያ ሊሆን ችሏል ብለዋል፡፡

አያይዘዉም  ከመንግስት ጎን ባለሀብቱ ጭምር በገንዘቡ እና በእዉቀቱ ዘመን ተሻጋሪ የልማት  ስራዎች በመሥራቱ በራስ አቅም  የመሥራት ባህል የፀናበትና ትዉልድ ሀብት መሆኑ የተረጋገጠበት ዘመን ማየት መቻላቸዉን ገልፀዉ በአጭር ጊዜ ዉስጥ መንግስትና ህዝብ ተጣምረዉ በሠሯቸዉ እጅግ አስገራሚ ዉጤታማ  ስራዎች መደመማቸዉንና  መደሰታቸዉን  ገልፀዋል።

በከተማዋ የተሠሩ እና በመሠራት ያሉ እነዚህ ፈርጀ ብዙ የልማት ስራዎች በእኛ በሀይማኖት አባቶች መጎብኘቱ እሰከ አሁን በተሰሩትና በቀጣይ ለሚሰሩ ዘላቂ የልማት ተግባራት እና ፈጣን የእድገት ጉዞ በትዉልዱ ላይ ለማስረፅ እና ለተቀረዉ ዓለም ለማስተዋወቅ ትልቅ ትርጉም ያለዉ ነዉ ብለዋል።

ፈጣሪ በባረካት ምድር በሀይማኖት አባቶች እየተባረኩ ለቀጣይ ትዉልድ የሚበጅ ስራዎችን መስራት ከመቻል በላይ የሚያስደስት ነገር  የለም ያሉት ጎብኚዎቹ በቀጣይም በሁለተናዊ መልኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታችን ነዉ ሲሉ ሃሳባቸዉን ገልፀዋል፡፡

አክለዉም ሀሳብ አመንጪዎችንና ሀሳብን ወደ ተግባር ለዉጠዉ  ለትዉልድ ትርጉም ያለዉ ተጨባጭ እድገት ላስመዘገቡ በዚህም መንግስትና ህዝብ ለሠሩት ታሪካዊ ስራ ከልብ ሊመሠገኑ እንደሚገባና ሁሉም ቤተ-እምነቶች  ይበልጥ በመሳተፍ አሻራቸዉን ማኖር ይጠበቃል ሲሉም በሰጡት አስተያየት መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.