በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ከቴክኒክና ሙያ ማሰ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የተወጣጡ አመራሮችና አሰልጣኞች የልማት ስራዎችን ጎበኙ።

በአዲስ አበባ ከሚገኙ የተለያዩ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት የተወጣጡ አሰልጣኞች በከተማዋ የተሰሩና እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በዛሬው  እለት  በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ  ኮሌጆች  የተወጣጡ   አመራሮችና አሰልጣኞች  የገላን ጉራ የተቀናጀ መንደር፣  የእንሰሳት ልማት ልህቀት ማዕከል፣ ቦሌ ቡልበላ ፓርክ፣ የለሚኩራ ገበያ ማዕከልና ሌሎች  ልማት  ስራዎችን  ጎብኝተዋል።

መንግስት እያከናወናቸው የሚገኙ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች በሚዲያ ከምናየው ባለፈ በተጨባጭ ተመልክተናል ያሉት
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች የተከናወኑ ስራዎች የነገ ሐገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት ጉልህ አስተዋጽኦ ያላቸው መሆኑን እና ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ የሚሰሩ የልማት ስራዎችን በአካል ተገኝቶ በመጎብኘት የሚጠበቅባቸውን  ኃላፊነት እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.