
“ጠንካራ የሲቪክ ማኅበራት ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ” በሚል መሪ ቃል በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ከሚገኙ ሲቪክ ማኅበራት ጋር ውይይት ተካሄደ
በውይይት መድረኩም ከሀገራዊው ለውጥ ማግሥት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራትና የተገኙ ስኬቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የሲቪክ ማኅበራትን ሚና የተመለከተ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሔዷል።
በሀገረ መንግሥት ግንባታ፣ በሰላም፣ በልማት፣ በመልካም አስተዳደር እና በሰው ተኮር ተግባራት መንግሥት እያከናወነ ያለውን ሁሉን አቀፍ ተግባር በመደገፍና የሕዝብ ተሳትፎን በማስተባበር ረገድ ሲቪክ ማኀበራት የማይተካ ሚና ያላቸዉ በመሆኑ ለተመዘገቡ ስኬቶች አበርክቶአቸዉ የላቀ እንደነበር በዉይይቱ ተመላክቷል።
በተጨማሪም የሲቪክ ማኀበራት በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የያዙ እንደመሆናቸው በሀገራዊው ለውጥ የተገኙ ስኬቶችን ይበልጥ ለማጠናከር ሲያደርጉ የነበረውን ሁለተናዊ እንቅስቃሴ በዘላቂነት እንዲያስቀጥሉ የተፈጠረዉን እድል መጠቀም እንደሚገባም ተገልጿል።
በሌላ በኩልም በማኅበራቱ በኩል የሚነሱ ጥያቄዎችን ከተማ አስተዳደሩ ትኩረት በመስጠት ህጋዊ መሠረትን ተከትሎ ደረጃ በደረጃ በተቀናጀ ህጋዊ አግባብ ምላሽ እየሠጠ መምጣቱ እና በቀጣይም ይኸዉ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ ተመላክቷል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት እንደሀገርም ሆነ ከተማ አቀፍ ደረጃ መንግስት ያከናወናቸዉን በርካታ እና ፈርጀ ብዙ ተግባራት የሀገርንና የትዉልድን እድገት በተጨባጭ የሚያረጋግጡ እና የቀጣይ ትዉልድን ብሩህ ዘመን አመላካች መሆናቸዉን ገልፀዉ ማህበራት ከዚህ አኩሪ ተግባር ጎን በመቆም የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡
በመጨረሻም መንግስት ለቪክ ማህበራት እያደረገ ያለዉን ድጋፍ አድንቀዉ ለሁለተናዊ ተጠቃሚነት በምናደርገዉ እንቅስቃሴ አሁንም የተጀመረዉ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸዉ ሲሉ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.