ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ምሽት በብሔ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ምሽት በብሔራዊ ቤተመንግሥት በተካሄደ ሥነሥርዓት የኢትዮጵያን ታላቁን የክብር ኒሻን ለቢል ጌትስ ሸልመዋል። ይኽ የከበረ ሽልማት የጌትስ ፋውንዴሽን ባለፉት 25 አመታት በኢትዮጵያ ላበረከታቸው አሻጋሪ ሥራዎች እና ታላላቅ ዘመን ተሻጋሪ በጎ ተፅዕኖዎችን ያከበረ ነዉ።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በንግግራቸው ለቢል ጌትስ ፋውንዴሽን የ25 አመታት አሸጋጋሪ ሥራዎችን ምስጋና አቅርበዋል። ቢል ጌትስ ከቴክኖሎጂ ፈር ቀዳጅነት ወደ በጎ አድራጊነት ያደረጉትን ጉዞ በማውሳትም ዝቅ ብሎ በማገልገል፣ በአክብሮት እና በእኩልነት እምነት ላይ የተመሠረተውን አገልግሎታቸውን አድንቀዋል። ፋውንዴሽኑ በጤና፣ ግብርና፣ ዲጂታል መታወቂያ የሚያደርገው ጥረት ብሎም ጠንካራው በመከባበር ላይ የተመሠረተ ትብብር በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ተወስቷል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.