"የገጠሩን ማህበረሰብ አኗኗር ለማሻሻል የተጀመረ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"የገጠሩን ማህበረሰብ አኗኗር ለማሻሻል የተጀመረው የገጠር ኮሪደር በሁሉም አካባቢዎች እየተስፋፋ ነው። በዛሬው እለትም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ሲንቢጣ ቀበሌ የገጠር ኮሪደር ልማት አካል የሆኑ ሞዴል የገጠር መንደሮች ግንባታን አስጀምረናል።

ሞዴል የገጠር መንደሮቹ ቀላል ወጪ የሚጠይቁና በአካባቢው በሚገኙ ግብዓቶች የሚገነቡ ሲሆኑ አርሶ አደሩም ጤናማና ክብር ያለው ህይወት እንዲኖር የሚያስችሉ ናቸው። 

በአካባቢው ከ2 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በመስኖ  የበቆሎ ምርጥ ዘር ብዜት እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት እየተካሄደ ሲሆን ከዚህ ቀደም በጎርፍና ድርቅ አደጋ ይታወቅ የነበረውን አካባቢ የልማት ተምሳሌት ያደርገዋል"።

ጠቅላይ ምኒስትር ዶክተር ዓብይ አሕመድ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.