
ዛሬ "ለተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓትና ባህል ግንባታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና" በሚል መርህ ሀሳብ ከአዲስ አበባ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር ተወያይተናል።
ከለውጡ ወዲህ እንደ ሀገርም ሆነ እንደ አዲስ አበባ ከተማ በገዢው ፓርቲና ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ያለው የፖለቲካ እሳቤ ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በሀገራዊ እና በከተማ አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ተግባቦት እየፈጠርን ተቀራርበን የመስራት ባህል እየገነባን ነው።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግሥት ስልጣንን ለመጨበጥ በህዝብ ይሁንታ ምርጫን ማሸነፍ እንዳለባቸው የሚታወቅ ቢሆንም፣ ፓርቲያችን ብልጽግና ስልጣን ከያዘ በኋላ አዲስ እና የላቀ የፖለቲካ ባህል መለማመድ አለብን ከሚል ቁርጠኛ አቋማችን የተነሳ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመንግሥት ካቢኔ ውስጥ ጭምር እንዲካተቱ ተደርገው አብረን በመስራት አዲስ የፓለቲካ ባህልን በተጨባጭ እየገነባን ነዉ።
በከተማችን የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮቹ የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ላከናወናቸው በርካታ የልማት ስራዎች አበረታተዉ፣ ይበልጥ ልናተኮርባቸው በሚገቡን ጉዳዮች ዙሪያም ገንቢ አስተያየቶች ሰንዝረዉ የተለያዩ የህዝቡን ፍላጐቶች መሰረት ያደረጉ ጥያቄዎችን አንስተዋል።
እኛም እንደ ከተማ አስተዳደር የጀመርነውን አዎንታዊ መስተጋብር ማሳለጥ እንዲሁም የህዝቡን ፍላጐቶች መሰረት ያደረጉ ስራዎችን በፍጥነት እና በጥራት መስራትን አጠናክረን እንደምቀጥል አረጋግጠንላቸዋል።
በመጨረሻም የፖለቲካ ምህዳርን ይበልጥ እያሰፋን ለሀገር ሰላም እና ልማት የሚጠቅሙ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን በትብብር እና በጋራ መስራተችንን አጠናክረን ለመቀጠል መግባባት ላይ ደርሰናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.