
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተከማዋ ዕድገት እየሰጡ ላሉት በሳል አመራር እውቅና ሰጠ
የጋራ ምክር ቤቱ ለከንቲባ አዳነች አቤቤ እውቅናውን የሰጠው የአዲስ አበባን ህዝብ ኑሮ በተጨባጭ የለወጡ ግዙፍ የልማት ስራዎችን ከጎበኙ በኋላ በዛሬው ዕለት ከከንቲባዋ ጋር በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ ነው።
የጋራ ምክር ቤቱ መሪዎች ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና መላው አመራራቸው የከተማዋን ዘላቂ ልማትን ታሳቢ ያደረጉ ግዙፍ ፕሮጄክቶችን በፍጥነት እና በጥራት በማከናወን ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ በመቻላቸው ያላቸውን አድናቆት የገለጹ ስሆን፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ልዩነቶቻቸውን በማክበር ለሀገር ሰላምና ልማት በጋራ መስራት እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.