የገጠር ኮሪደር ልማት ሀገርን የመለወጥ ሰፊ ራዕ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የገጠር ኮሪደር ልማት ሀገርን የመለወጥ ሰፊ ራዕይ የተሰነቀበት ሀገራዊ ውጥን ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የገጠር ኮሪደር ልማት ሀገርን የመለወጥ ሰፊ ራዕይ የተሰነቀበት ሀገራዊ ውጥን መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከንባታ ዞን አዲሎ ዙሪያ ወረዳ ሀሚዶ ቀበሌ የገጠር ኮሪደር ልማትን ማስጀመራቸውን በማኀበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።

በተጨማሪም በቀበሌው የሚኖረው አንድ የአርሶ አደር ሞዴል የገጠር መንደርን የጎበኙ ሲሆን፣ አርሶ አደሩ ጽዱ፣ ጤናማና ለማየት እጅግ ማራኪ የሆነ የመኖሪያ አካባቢን በመኖሪያ ግቢው ውስጥ በመፍጠር ምሳሌ የሚሆን ስራ አከናውኗል ብለዋል።

ጽዱ የመኖሪያ ስፍራን ከመፍጠር ባለፈ በሌማት ትሩፋትና ጓሮ አትክልት ልማት ላይም ንቁ ተሳተፎ እያድረገ ይገኛል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ስራ በሁሉም አካባቢ በትብብር ሊሰፋ እንደሚገባ ገልጸዋል።

እንዲሁም በዞኑ ልዩ የተፈጥሮ ገጸ በረከት የሆነው ሀምበርቾ ተራራን በማህበረሰብ ተሳትፎ የኢኮ ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተከናወኑ ስራዎችም እጅግ የሚደነቁ ናቸው ነው ያሉት።

በተራራው የተገነባው 777 የመወጣጫ ደረጃ አካባቢውን ተደራሽ የመስህብ ስፍራ ያደረገው መሆኑን የገለፁ ሲሆን፣ ተራራ መውጣትና የተለያዩ የአእዋፋት ዝርያዎችን መመልከት የሚወዱ ቱሪስቶች ወደ እዚህ ስፍራ በመምጣት ማራኪ ጊዜን ማሳለፍ እንደሚችሉ አመላክተዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.