
"ያለምንም ምክንያት ሸቀጦች ላይ የተጋነነ ዋጋ በመጨመር ህዝቡን ምሬት ውስጥ የሚያስገቡ ህገ-ወጥ የንግድ ተዋናዮችን ለመቆጣጠር የተቀናጀና የተናበበ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የህግ የበላይነትን እናስከብራለን"ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ የበላይነትና ቁጥጥር ንኡስ ኮሚቴ አሁናዊ የገበያ ሁኔታን ማእከል ያደረገ ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምቷል ።
በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሊድያ ግርማ እንደተናገሩት ያለምንም በቂ ምክንያት ሸቀጦች ላይ የተጋነነ ዋጋ በመጨመር ህዝቡን ምሬት ውስጥ የሚያስገቡ የህገ-ወጥ ነጋዴዎች ተግባር ለመከላከል የተቀናጀና የተናበበ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የህግ የበላይነትን እናስከብራለን ብለዋል።
ቢሮ ሀላፊዋ አክለዉም ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ በህገ ወጥ መንገድ በሚንቀሳቀሱ አምራቾች፣ አስመጪዎች፣ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች ላይ የተቀናጀና የተናበበ የቁጥጥር ሥራ መሥራት፣ የገበያ ማዕከላትን ከደላላ ነፃ በሆነ መልኩ የንግድ ሥራው እንዲካሄድ ማድረግ፣ ምርት በሚከዝኑት አካላት ላይ ጥብቅ ፍተሻ፤ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፣ የነዳጅ ማደያዎች መከታተልና መቆጣጠር፣ ኮንትሮባንድን መቆጣጠር፤ የቅዳሜና የእሁድ ገበያ ማዕከላት በወጣው ተመን እንዲሸጡ መከታተል፣ በቅርቡ በፀደቀው ደንብ መሰረት እስከ የንግድ እንቅስቃሴ እስከ ምሽቱ 4:00 ክፍት ሆነው አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ፣ ኢ-መደበኛ ነጋዴዎች የመደበኛ ነጋዴዎችን መብት ሳይጋፉ በህግና ደንብ መሠረት እንዲሠሩ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል። ህግ የማስከበርና የቁጥጥር ስራዉ በቅንጅት እንዲሰራ አበክረዉ አሳስቧል።
የአዲስ አበባ የንግድ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሐቢባ ሲራጅ በበኩላቸውበዚህ ወቅት እንደተናገሩት ከዚህ በፊት በቅንጅት በሰራናቸው ሥራዎች ውጤት አምጥተናል።ነገር ግን አሁን በከተማው ላይ በሸቀጦች ላይ ያለምንም ምክንያት ሀገር ዉስጥ በሚመረቱ ምርቶች ሳይቀር ዋጋ የሚጨምሩ የንግዱ ማህበረሰብ ተዋናዮች መኖራቸዉን ባደረግነዉ ጥናት ችለናል። በመሆኑም በእነዚህ አካላት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ጠቅላይ መምሪያ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በበኩላቸው የመሠረታዊ ሸቀጦች ጉዳይ የመኖርና ያለመኖር የህልዉና ጉዳይ በመሆኑ በነዚህ ሸቀጦች ላይ ያለበቂ ምክንያት ዋጋ በሚጨምሩ ሕገ-ወጥ ነጋዴዎችና ደላሎች ላይ በመረጃ ላይ የተደገፈና የተቀናጀ የሕግ ማስከበር ሥራ ይሠራል ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.